Raxio DRC በ2022 ዓ.ም ሥራ ይጀምራል።

Raxio DRC በአገሪቱ የመጀመሪያው የኒውትራል አስተላላፊ Tier III የዳታ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ሲሆን ለአገሪቱ የዲጂታል ሽግግር ድጋፍ ከማድረጉም በተጨማሪ በአለም አቀፍና በአገር ውስጥ ግንኙነት መካከል ያለውን ክፍተት ይዘጋል።

መገኛ ቦታ

ኪንሻሳ
ከሴንትራል ቢዝነስ ዲስትሪክት/ Central Business District በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኝ

ግንኙነት

የTier III ደረጃ
እስከ 400 ራኮች
በአንድ ራክ 2 – 21 kW

ኢንዱስትሪዎች

ቴሌኮሞች
የፋይናንስ አገልግሎቶች
ድርጅቶች
ISPዎች
CDNኖች

ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ /DRC/ በቀጣዮቹ አመታት ውስጥ በአዳዲስ ከባህር በታች የኬብል ዝርጋታዎች እና የአገር ውስጥ ወሰን ተሻጋሪ የፋይበር ኔትወርኮችን በማስፋፋት የዲጂታል ምርት ውጤቶችና አገልግሎቶች ፍላጎት በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያድግ የተተነበየባት ከአፍሪካ ትላልቅና ፈጣን እድገት እያሳዩ ካሉ ገበያዎች መካከል አንዷ ነች።

የግንኙነት አገልግሎቶች

በ2022 ዓ.ም 2ኛ ዕሩብ አመት ስራውን ሲጀምር Raxio DRC ለደንበኞች ለአይቲ መሳሪያቸው በከፍተኛ ደረጃ ጥራቱን የጠበቀ፣ ተገጣጣሚ አገልግሎት የያዘ፣ በተሟላ ሁኔታ ለኢንዱስትሪ ተመራጭ ቴክኖሎጂን የያዘ፣ አስተማማኝ ደህንነት ያለው፣ ለAC/DC ሀይል ተስማሚና የማይቆራረጥ የያዘ የዲጂታል አገልግሎት ያቀርባል። Raxio DRC የሀገር ውስጥ የይዘት አቅራቢዎች የትራፊክ ፍሰትን ከማመቻቸት በተጨማሪ ለሁሉም የዲጂታል ተጠቃሚዎች የኢንተርኔት አገልግሎትን ፈጣን፣ የበለጠ አስተማማኝና በተመጣጣኝ ዋጋ የሚገኝ ያደርጋል።

የቦታ ለቦታ ግንኙነት

ስለ እኛ

ኒውትራል አስተላላፊ የዳታ ማዕከላችን አላማ ተኮር ሆኖ የተገነባ እና የተረጋገጠ የTier III ደረጃዎች ያሉት እንዲሁም 99.99% የአየር ሰዐት እና ተመራጭ ደረጃ ያለው መሳሪያ የሚያቀርብ ማዕከል ነው።

ማዕከላን ሁሉንም ለተልዕኮ ወሳኝ የአይቲ መሰረተ ልማቶች በቀን ለ24 ሰዐት/በሳምንት ለ7 ቀናት ያለ ምንም መቆራረጥ ለማስተናገድ እንዲቻል ለደንበኞች ተመጣጣኝ ዋጋ ያለው፣ አስተማማኝ የቦታ ለቦታ ግንኙነት የሚያቀርብ እና እስከ 400 ራኮች የሚያስተናግዱ ቦታዎችን የሚያቀርብ አገልግሎት መስጫ ነው።

ኒውትራል አስተላላፊ

ደንበኞችን ከተለያዩ አስተላላፊዎች ጋር እንዲገናኙ እና ከአስተላላፊዎች መካከል እንዲመርጡ ያስችላቸዋል።

የTier III ደረጃዎች

በቀን ለ24 ሰአት/በሳምንት ለ7 ቀናት ያልተቆራረጠ አገልግሎትን ለማረጋገጥ ያለ ምንም የመቆራረጫ ቦታ ተከታታይና ያልተቆራረጠ አገልግሎት ያቀርባል።

ተገጣጣሚ

በአገልግሎት መስጫው ውስጥ ፍላጎቶች በሚጠይቁት መሰረት እያደገ ከሚሄድ አቅም ጋር ወቅታዊና የወደፊት የደንበኞች ፍላጎቶችን ለማሟላት የተዘጋጁ ባለ ፌዝ አቅም ጥቅል መስመሮች።

PUE

1.3 የዲዛይን PUE ረሺዮ

ማቀዝቀዣ

ሀይል ቆጣቢ የአስተላላፊ መያዣ ያለው በተዘዋዋሪ ሙቀት እንዳይጨምር የሚያደርግ የማቀዝቀዣ ቴክኖሎጂ።

የሀይል ስርጭት

በባስባሮች ሀይል በሚያገኙ ተያያዥ ተሰቃይ መስመሮች አማካኝነት የሚደረግ የሀይል ስርጭት

የሀይል ዴንሲቲ

በአንድ ራክ ከ1 kW እስከ 21 kW ራኮችን የማስተናገድ አቅም ያለው

ራኮች

እስከ 58U. ተስማሚ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን የሚያቀርቡ መደበኛ 600 x 1200 ሚሜ ራኮች

ቁጥጥር

ከፍተኛ አፈጻጸምን ለማረጋገጥ እና ብልሽቶችን ፈልጎ ለማግኘት በቀን ለ24 ሰዐት/በሳምንት ለ7 ቀናት የሚደረግ NOC

ደህንነት

የሳይት ላይ ደህንነትን ለማረጋገጥ በቀን ለ24 ሰዐት/በሳምንት ለ7 ቀናት የሚደረግ የCCTV ቁጥጥር። በመግቢያና ሰርቨሮች መካከል እስከ 7 ዙሮች የሚሰራ አካላዊ ደህንነት።

ታሪካችን

የRaxio የዳታ ማዕከል የድርጅት ደረጃ ያለው የዳታ ማዕከል ሲሆን በኪንሻሳ፣ ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ /DRC/ በቅርቡ ስራ ይጀምራል።

Raxio በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ /DRC/ የመጀመሪያውን ድርጅት እና የአስተላላፊ ደረጃ ያለው የዳታ ማዕከል አገልግሎት መስጫን ያንቀሳቅሳል። Raxio የተመሰረተው በ2018 ዓ.ም በመላው ምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ የዲጂታል ኢኮኖሚ መሰረት ለመጣል የተቋቋመው የRoha Group ኩባንያ በሆነው በFirst Brick Holdings (“FBH”) ነው። Roha በመላው አፍሪካ አዳዲስ የንግድ ድርጅቶችን የሚገነባና የሚያቋቁም የUS Greenfield የኢንቨስትመንት ኩባንያ ነው።

በ2020 ዓ.ም ዕለታዊ የኢንተርኔት ትራፊክ በዕጥፍ ከመጨመሩና በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ አብዛኞቹ ኩባንያዎች ወደ ዲጂታል ውጤቶችና አገልግሎቶች እየተቀየሩ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የRaxio የዳታ ማዕከል የአገሪቱን የዲጂታል እድገት በተመጣጣኝ ዋጋ በሚቀርብ፣ ከፍተኛ የጥራት ደረጃ ያለው፣ የቦታ ለቦታ ግንኙነት ያለው የዳታ ማዕከል ለመደገፍ ወሳኝ እና በአገሪቱ የዲጂታል መሰረተ ልማት ውስጥ የጎደለ አስፈላጊ የዲጂታል አገልግሎት ያቀርባል።

የዳታ ማዕከሉ በአገር ውስጥ የይዘት አቅራቢዎችና አለም አቀፍ መካከል ያለውን የኢንተርኔት ፍሰት ያመቻቻል እንዲሁም የኢንተርኔት አገልግሎትን ለሁሉም ኮንጓውያን የዲጂታል ተጠቃሚዎች ፈጣን፣ የበለጠ አስተማማኝና በቀላል ዋጋ የሚገኝ ያደርጋል። ማዕከሉ በ2022 ዓ.ም ስራ ሲጀምር Raxio DRC በኒውትራል አስተላላፊነት የሚሰራና በሙሉ አቅሙ መስራት ሲጀምር እስከ 400 ራኮችን የማስተናገድ አቅም ያለው በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ በአይነቱ የመጀመሪያ፣ ብቸኛ የTier III ማረጋገጫ ያለው የአገልግሎት መስጫ ሆኖ ያገለግላል።

ተጨማሪ መረጃ ያግኙ

ያኒክ ሱካኩሙ/Yannick Sukakumu

ዋና ሥራ አስያጅ፣ ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፑብሊክ/DRC

ያኒክ/Yannick የRaxio DRC ዋና ሥራ አስኪያጅ ሲሆኑ በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ ውስጥ የRaxioን አገልግሎት መስጫዎች የማልማትና አሰራራቸውን የማስተዳደር ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል። ያኒክ/Yannick በቴሌኮሞች፣ የቴኖሎጂና የፋይናንስ ኢንዱስትሪዎች ዘርፎች የ12 ዓመታት የፋይናንስና ስትራቴጂ የስራ ልምድ አዳብረዋል።

ያኒክ/Yannick ወደ Raxio ከመምጣታቸው በፊት  በGroup Vivendi Africa የEastern DRC ክፍለ አህጉራዊ ዳይሬክተር ሆነው አገልግለዋል። ከዚህ ቀደም ብሎም በBboxx Capital የGoma የኦፕሬሽኖች ዳይሬክተር ሆነው ሰርተዋል። ያኒክ/Yannick በተጨማሪም በBharti Airtel DRC በተለያዩ የፋይናንስ፣ የንግድና የስትራቴጂ የስራ ድርሻዎች ላይ ሰርተዋል።

 

ያኒክ/Yannick ከኮንጎ Universitie Protestante በኢኮኖሚክስ የመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቁ ሲሆን ቀጥለውም ከፍራንክፈርት የንግድ ስራና አስተዳደር ትምህርት ቤት/ Frankfurt School of Business and Management በማይክሮፋይናንስ ሁለተኛ ዲግሪ/ማስተርስ ዲግሪ/ አግኝተዋል።

አዳዲስ ዜናዎች

ኤክስፐርቶቻችን/ሙያተኞቻችንን ያናግሩ

ስለ አገልግሎቶቻችን እና የራሲዮ የዳታ ማዕከላት/Raxio Data Centres እንዴት ለንግድ ስራዎ ድጋፍ ሊያደርጉልዎ እንደሚችሉ በተመለከተ የበለጠ ማወቅ ይፈልጋሉ? ለጥያቄዎችዎ በደስተኝነት መልስ ለመስጠት ዝግጁ ነን። ቅጾቹን ይሙሉ እና በተቻለ ፍጥነት እናገኝዎታለን።