አገልግሎቶች

የአፍሪካ መሪ የዳታ ማዕከል አገልግሎቶች

የአፍሪካ መሪ የዳታ ማዕከል አንቀሳቃሽ እንደመሆናችን ከጥግ እስከ ጥግ የሚደርስ የአይቲ መሰረተ ልማት አስቸተዳደርና የስምሪት ድጋፍ እናቀርባለን። ሙያዊ ልምዳችን ቁጥጥር ከሚደረግባቸው የቦታ ለቦታ በመስመር ማገናኘት እና የደንበኛ መገኛ ቦታዎች ተደራሽትን ጨምሮ ሁሉንም ነገር ያጠቃልላል።

ልዩ ሙያዊ እውቀታችን እና ያልተነካ የመሰረተ ልማት እምቅ አቅማችን ለደንበኞቻችን እጅግ ተፈላጊ መስፈርቶችን ለማሟላት በልክ የተሰሩ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን እና አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ድጋፍ እናቀርባለን።

የቦታ ለቦታ ግንኙነት

ሁሉም የዳታ ማዕከሎቻችን የሚገነቡት በTier III ደረጃዎች ሆኖ እርስዎ 99.99% ያልተቆራረጠ የአየር ሰዐት እንዲያገኙ ለማረጋገጥ ተመራጭ ደረጃውን የጠበቀ መሳሪያ ያቀርባሉ።

ደንበኞቻችን ሁሉንም የተልዕኮ ወሳኝ የአይቲ መሰረተ ልማት ለማግኘት በተመጣጣኝ ዋጋ ከምናቀርባቸው፣ አስተማማኝ እርስ በርሳቸው የተገናኙ ቦታዎች እና ማስተላለፊያዎች ተጠቃሚ ይሆናሉ።

ዋና ዋና ባህሪያት/አገልግሎቶች የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ:

 • የኬሪየር ኒውትራል አገልግሎቶች ደንበኞችን ከተለያዩ አስተላላፊዎች እና የቦታ ለቦታ ግንኙነት ያላቸው አቅራቢዎች ጋር እንዲገናኙ እና ከእነዚህ መካከል እንዲመርጡ ያስችላሉ፤ ከፍተኛ ደረጃ ተለዋዋጭ እና አጠቃላይ አገልግሎቶችን ያቀርባሉ።
 • በTier III ደረጃዎች ላይ የተሰሩ ያለ ምንም የመቋረጫ ነጥቦች የ24/7 ተከታታይ አገልግሎት ማግኘትን ያረጋግጣሉ።
 • ተቀያያሪ አገልግሎት መስጫዎች ለወቅታዊ እና እያደጉ የሚሄዱ የወደፊት ፍላጎቶች እንደመጥኑ ተደርገው የተዘጋጁ።
 • ዝቅተኛ ሀይል የመጠቀም ውጤታማነት ምጣኔው በከፍተኛ ደረጃ ሀይል ቆጣቢ በሆኑ ዲዛይኖች የተደገፈ ነው።
 • የሀይል ዴንሲቲዎች ከ 1kW እስከ 21kW ድረስ የተለያዩ የአፈጻጸም ፍላጎቶችን ለመደገፍ
 • 600 x 1200mm ራኮች እስከ 55U ደረጃ

ተሸጋጋሪ ግንኙነት

የተሸጋጋሪ ግንኙነት የኬብል አገልልግሎቶቻችን ከአስተላላፊዎች፣ ድርጅቶች፣ የይዘት አከፋፋዮች እና የክላውድ አገልግሎት አቅራቢዎች ጋር ፈጣን፣ ቀላል እና ቀጥተኛ ግንኙነቶች እንዲያደርጉ ያስችሉዎታል። ለዚሁ አላማ በተዘጋጀ CAT5/6 እና ፋይበር አማካኝነት በተቻለ ፍጥነት ግንኙነትዎን በከፍተኛ ደረጃ እንዲያሳድጉና የንግድ ስራዎን እንዲያሳድጉ እናስችልዎታለን።

የሚከተሉትን እናቀርባለን:

 • የተለያዩ የቤት ውስጥ የMeet Me ክፍሎች ግንኙነት
 • ለአቻም ሆነ አቻ ያልሆኑ አባላት የሚያገለግሉ የኢንተርኔት ልውውጥ ቦታዎች ግንኙነት
 • ደንበኞችን ከዳታ ማዕከል ጋር የሚያገናኝ ግንኙነት
 • የተመደቡ የግል መደብ ቻናሎች/ማሰራጫዎች

ፈጣንና ጥቁር ፋይበር

ተቀባይ አስተላላፊዎቻችን በዳታ ማዕከሎቻችን ሰፊና ተከታታይ የግንኙነት መስመሮች ታግዘው ከፍተኛ SLA በመሸከም ፈጣን የፋይበር አገልግሎቶችን ያቀርቡልዎታል። አስተላላፊዎቻችን ከቦታ ቦታ እና ከአንድ ቦታ ወደተለያዩ ቦታዎች ግንኙነት ያቀርባሉ፣ የሀይል ሰርኪዩቶችን ከዳታ ማዕከሎቻችን ወደ ሌሎች በርቀት የሚገኙ ቦታዎች ያስተላልፋሉ።

በፋይበር ኬብል ሁለቱም ጫፎች የራሳቸውን ፈጣን መሳሪያ የማቅረብ ችሎታና አቅም ላላቸው ደንበኞች አገልግሎቶቹን፣ ሀይሉን እና መስመሩን ሙሉ በሙሉ እንዲቆጣጠሩ ለማስቻል የጥቁር ፋይበር ኔትወርኮችን ልናመቻችላቸው እንችላለን።

የርቀት ድጋፍ

የሰለጠኑ መሀንዲሶችን የያዘው ቡድናችን ባስፈለግዎ ጊዜ ሁሉ የቴክኒክ ድጋፍ ለማቅረብ በቀን ለ24 ሰአት በሳምንት ለ7 ቀናት ይሰራል። አገልግሎቶችን ከየትኛውም የአለም ክፍል ሆነው በተሳለጠ አኳኋን በማግኘት ረገድ የአእምሮ ሰላም የሚሰማዎ ለዚህ ነው።

ጎጆ

ለወሳኝ የአይቲ መሰረተ ልማታቸው ሌላ ተጨማሪ አካላዊ የደህንነት ደረጃ ለመጨመር ለሚፈልጉ ደንበኞች በብረት የተሰሩ፣ የግል ከለላ የተሰራላቸው ጎጆዎቻችን ለራኮችዎ የተጣበበ የአየር ሰአት ደህንነት ለማቅረብ ተመራጭ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ናቸው።

በተጨማሪም እንደ 24/7 CCTV፣ የአሻራ ማማጋገጫ፣ ባለ ሁለት መደብ መግበያና ሌሎችም የመሳሰሉ በእነዚህ ጎጆዎች ላይ የደህንነት ባህሪያት መጨመሪያዎችንም ያገኛሉ።

የደንበኛ ቦታዎች

ለደንበኞቻችን ከዳታ ማዕከሎቻችን ሆነው እንዲሰሩ ለመርዳት የግል የስራ ቦታዎች እናቀርባለን። እነዚህ የስራ ቦታዎች ዴስኮችን፣ የስብሰባ ክፍሎችና ትላልቅ የማደሪያ ክፍሎችን ይይዛሉ።

ጭኖ መቀየር

የሙያተኞች ቡድናችን የመቀየር ሂደቱን በራሱ በማጠናቀቅ መሳሪያዎን ወደ ዳታ ማዕከሎቻችን ለማጓጓዝ የሚያጋጥሙዎትን ወከባና የእንቅስቃሴ ስጋት ለማስቀረት ይሰራል። ይህ ህይወትዎን ከማቅለል ባለፈ ለአይቲ መሰረተ ልማት ተከላ የሚጠፋን ጊዜ እና መወሳሰብ ለመቀነስ ያግዛል።

የሶስተኛ ወገን አገልግሎቶችን ማግኘት

Raxio በዳታ ማዕከላቱ የንግድ ስራ ለመስራት አስቻይ ድርጅት ነው። በአገልግሎት መስጫዎቻችን ውስጥ የሚከተሉትን ጨምሮ በሌሎች ደንበኞች የሚቀርቡ ተጓዳኝ የሶስተኛ ወገን አገልግሎቶችን ያገኛሉ፡

 1.  የግንኙነት አገልግሎቶች
 2. የክላውድ በኮምፒውተር የሚሰሩ አገልግሎቶች፤ ለምሳሌ፡
  – የሶፍትዌር አገልግሎት
  – የመሰረተ ልማት አገልግሎት
  – የፕላትፎርም አገልግሎት
  – የመጠባበቂያ ቋት
 3. ከአደጋ ማገገሚያ
 4. የሳይበር ደህንነት
 5. የይዘት ስርጭት

ኤክስፐርቶቻችን/ሙያተኞቻችንን ያናግሩ

ስለ አገልግሎቶቻችን እና የራሲዮ የዳታ ማዕከላት/Raxio Data Centres እንዴት ለንግድ ስራዎ ድጋፍ ሊያደርጉልዎ እንደሚችሉ በተመለከተ የበለጠ ማወቅ ይፈልጋሉ? ለጥያቄዎችዎ በደስተኝነት መልስ ለመስጠት ዝግጁ ነን። ቅጾቹን ይሙሉ እና በተቻለ ፍጥነት እናገኝዎታለን።

ቆይ በናተህ...
ሁሉም ተጠናቀቀ!
ውይ! የሆነ ስህተት ተከስቷል. እባክዎ ዳግም ይሞክሩ.