ስለ Raxio በተመለከተ

ሙያዊ ልምዳችን

Raxio Group ተመራጭ የቦታ ለቦታ፣ ወሰን ተሻጋሪ ግንኙነት፣ የፋይበርና አይቲ መሰረተ ልማት አገልግሎቶችን የሚያቀርብ የአፍሪካ መሪ የኬሪየር ኒውትራል የዳታ ማዕከል አንቀሳቃሽ ነው። በአካባቢያዊ የገበያ እውቀታችን እና አለም አቀፍ የኢንዱሰስትሪዎች ሙያተኞቻችን እና አጋሮቻችን እየታገዝን ለአፍሪካ የዲጂታል ኢኮኖሚ በመሰረት ጣይነት የሚያገለግሉ እርስ በርሳቸው በኔትወርክ የተገናኙ የዳታ ማዕከላትን ገንብተን እናንቀሳቅሳለን።

የዳታ ማዕከሎቻችን ለፈጠራ የቴክኒክ መሰረቶችን የሚያቀርቡ አላማ ተኮር መሰረተ ልማት ከመሆናቸውም በተጨማሪ ለአፍሪካ ኢኮኖሚ እድገትና ወደ ዲጂታል ሽግግር ድጋፍ የሚያደርጉ የመሰረተ ልማት ድርጅቶች ናቸው።

ባህላችን

የአፍሪካ ሰፊ የዲጂታል ተጠቃሚ ማህበረሰቦች የሞባይል ስልክ አጠቃቀም እያደገ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የዳታ ፍጆታና ፍላጎትም በአስገራሚ ፍጥነት እያደገ ይገኛል። ይህን ዲጂታል ኢኮኖሚ ለመደገፍ እና በደንበኞች የሚፈለጉ ፍላጎቶችና አገልግሎቶችን ለማቅረብ ለድርጅቶች እጅግ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ አስተማማኝ እና ከፍተኛ አፈጻጸም ያለው የዳታ ቋት/ማዕከልና ማቀነባበሪያ ማቋቋም እንደሚያስፈልጋቸው እናምናለን።

ለአፍሪካ የዲጂታል ሽግግር አቅም መፍጠር

የRaxio Group የዳታ ማዕከላት በአይነታቸው በክፍለ አህጉሪቱ የመጀመሪያ ናቸው። የTier III አገልግሎት መስጫዎቻችን ለተልዕኮ ወሳኝ የሆኑ ሲስተሞች በከፍተኛ ደረጃ አስተማማኝ ለማድረግ 99.99% ያልተቆራረጠ የአየር ሰአት ይሰጣል። ደንበኞች አስተማማኝ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ተከታታይ የ24/7 አገልግሎት ማግኘት መቻላቸውን በማረጋገጥ ከፍተኛ ጥራት ያለው መሳሪያና ሙያዊ ቁጥጥር የሚደረግባቸው አገልግሎት መስጫዎች እናቀርባለን። እንደ ኬሪየር ኒውትራል የዳታ ማዕከላት በተጨማሪም ሁሉንም አይነት መስፈርቶች ለማሟላት ለደንበኞች የተለያዩ አይነት የግንኙነት አማራጮችን እናቀርባለን።

በRaxio Group ባለፉት 3 አመታት ውስጥ መዳረሻዎቻችንን እያስፋፋን ከመሆኑም በተጨማሪ በመላው አህጉሪቱ ውስጥ ከ10-12 አገልግሎት መስጫዎች ለመገንባት በሂደት ላይ ነን። የዳታ ማዕከላቶቻችን የሚቋቋሙት በመላው አፍሪካ የሚደረገውን የኢኮኖሚ እድገት፣ ማህበራዊ ልማትና የዲጂታል ትራንፎርሜሽን ለማስቀጠል ነው።

ሮበርት ሙሊንስ/ Robert Mullins

ፕሬዝዳንት

ሮበርት/Robert የRaxio Group ባለቤት የሆነው የFirst Brick Holdings ኩባንያ ፕሬዝዳንት ናቸው። ሮበርት/Robert በመላው አፍሪካ ለRaxio የዳታ ማዕከላት ስትራቴጂያዊ የእቅድ ዝግጅት፣ የማዕከላቱ መስፋፋትን የመምራት ኃላፊነት የተሰጣቸው ከመሆኑም በተጨማሪ ቡድኑ ከአለም አቀፍ እና ክፍለ አህጉራዊ ደንበኞችና አጋሮች ትስስር ጋር የሚያካሂደውን ግንኙነት ያስተዳድራሉ።

ሮበርት/Robert በተጨማሪም በአፍሪካ በመላ አህጉሪቱ በአዳዲስ ኩባንያዎች ላይ ኢንቨስት በማድረግና በመገንባት ትርፋማ የንግድ ድርጅቶችን የሚያቋቁም የዩኤስ ድርጅት የሆነው የRoha Group አጋር ናቸው። Roha ከ2018 ዓ.ም መግቢያ ጀምሮ በRaxio Group ስር የኢንቨስትመንት ልማትe በማቋቋም እየመራ ይገኛል።

Roha እና Raxio ከመቀላቀላቸው አስቀድሞ ሮበርት/ Robert የConfidex፣ የከፍተኛ የቴክኖሎጂ እድገት ኩባንያ የሆነው የSmart Mobility የንግድ ድርጅት ዋና የፋይናንስ ኦፊሰር እና ኃላፊ የነበሩ ከመሆኑም በተጨማሪ የትራንስ አትላንቲክ ሽርክና ድርጅት የሆነው የLogispring አጋር የነበሩ ሲሆን በድርጅቱ የተለያዩ የፖርትፎሊዮ ኩባንያዎች ውስጥ በቦርድ አባልነት አገልግለዋል። ሮበርት/ Robert የባንክ ስራ ኢንቨስት ማድረግ ሙያቸውን የጀመሩት በSchroder Salomon Smith Barney ነበር።

ሮበርት/ Robert ከለንደን የኢኮኖሚክስ ትምህርት ቤት/ London School of Economics በምርምር ስራዎች በማዕረግ በኤምኤስሲ የተመረቁ ከመሆኑም በተጨማሪ ከዳርትማውዝ ኮሌጅ/Dartmouth College በምህንድስና የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል።

ማርኮ አንጄሊኖ/Marco Angelino

የቡድን የፋይናንስ ኦፊሰር

ማርኮ/Marco የቡድን የፋይናንስ ኦፊሰር ሲሆኑ በሀይል ልማት፣ መሰረተ ልማት እና የባንክ ኢንዱስትሪዎች ውስጥ የ15 አመታት ሙያዊ ልምድ አላቸው።

የማርኮ/Marco ሙያዊ ልምድ በተለያዩ የንብረት ምድቦች (ለምሳሌ፡ ታዳሽ ሀይል፣ የክፍያ መንገዶች፣ የባቡር ትራንስፖርት፣ ወዘተ) ስር አጠቃላይ የኢንቨስትመንት እሴት ሰንሰለትን እና የተለያዩ ጂኦግራፊያዊ ቦታዎችን (አፍሪካ፣ አውሮፓ፣ ዩኤስኤ፣ ላቲን አሜሪካ) ያጠቃልላል። ማርኮ/Marco በካፒታል ማስገኛ (ብድርና ኢኩዊቲ)፣ M&A፣ እና ስኬታማ አለም አቀፍ ቡድኖችን በማቋቋም ረገድ ደማቅ የኋላ ታሪክ አላቸው።

ማርኮ/Marco በ2016 ዓ.ም ከSDA Bocconi School of Management (ሚላን፣ ጣሊያን) በGlobal Executive MBA አግኝተዋል።
ማርኮ/Marco በባንኪንግና ፋይናንስ PhD አጠናቀዋል።

ሮበርት ሳውንደርስ/Robert Saunders

የቡድን ዋና የቴኖሎጂ ኦፊሰር

ሮበርት/Robert የRaxio የቡድን ዋና የቴክኖሎጂ ኦፊሰር ሲሆኑ  ለRaxio የዳታ ማዕከል አገልግሎት መስጫዎች የዲዛይን፣ ግንባታ፣ ስራ ማስጀመርና አሰራር ስራዎች ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል። ሮበርት/Robert ለዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉጉት ያላቸው እና በልህቀት መልካም ስም ያተረፉ ሲሆን በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ኢንዱስትሪ ከ17 ዓመታት በላይ የስራ ልምድ አላቸው።

ሮበርት/Robert ወደ Raxio ከመቀላቀላቸው በፊት በSyska Hennessy Group፣ MENA የንግድ ስራ ክፍል ስራ አስኪያጅ ሆነው ሰርተዋል። በአገልግሎት ዘመናቸው ሮበርት/Robert በተለያዩ የስራ መስኮች አሸናፊ የሆኑ ቡድኖችን የመምራት ተፈጥሯዊ ችሎታ እንዳላቸው አሳይተዋል። Syska በሮበርት/Robert ቁርጠኛ አቋም እና አሰራርን ማዕከል ያደረገ ትኩረት ታግዞ በመካከለኛው ምስራቅ ውስጥ የላቀ የዳታ ማዕከል አማካሪ ድርጅት ለመሆን በቅቷል።

ሮበርት/Robert ከሴንተርበሪ ክራይስት ቸርች ዩኒቨርሲቲ/ Centerbury Christ Church University በሜካኒካል ምህንድስና ዲግሪ አግኝተዋል።

ጁዲ እንጉሩ/ Judy Nguru

የስትራቴጂክ ልማት ምክትል ፕሬዚዳንት

ጁዲ/Judy የራክሲዮ/Raxio ቡድንን የመስፋፋት እና የዕድገት ስትራቴጂዎችን ለማስፈጸም በሃላፊነት የሚያገለግሉ ከፍተኛ የስትራቴጂክ ልማት ምክትል ፕሬዚዳንት ናቸው። በሙያቸው ከፍተኛ ልምድ ያካበቱ ባለሙያ ሲሆኑ፣ በቴክኖሎጂ፣ በቴሌኮሙኒኬሽን፣ በ FMCG እና በፋይናንስ ዘርፎች ከ16 ዓመታት በላይ ልምድ ያላቸው ባለሙያ ናቸው።

ወደ ራክሲዮ/Raxi ከመቀላቀላቸው ቀደም ብሎ፣ ቀድሞ የ Google ፕሮጄክት ሊንክ ለነበረው CSquared የቡድን ቢዝነስ ዴቨሎፕመንት ስራ አስኪያጅ ሆነው ያገለገሉ ሲሆን፣ በዚህም ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ አዳዲስ ገበያዎችን በማስፋፋት በስራ ዘመናቸው ስድስት አዳዲስ ገበያዎችን በተሳካ ሁኔታ ማቋቋም ችለዋል። ጁዲ/Judy ዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን በማፋጠን እና ሁሉንም ሰራተኞች አካታች የሆነ የስራ ባህልን በመፍጠር ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ ለውጥ ለመፍጠር በመላው አፍሪካ ያለውን ጥምረት ለማፋጠን በትጋት ይሰራሉ።

ጁዲ/Judy በፊላደልፊያ፣ ፔንስልቬንያ፣ ዩኤስኤ ከሚገኘው ላ ሳሌ ዩኒቨርሲቲ/La Salle University በማኔጅመንት የ MBA ዲግሪ ያላቸው ሲሆን፣ በፈረንሳይ አገር ከሚገኘው የፓሪስ የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲ/American University of Paris በዓለም አቀፍ ንግድ BA ዲግሪ አላቸው። ከዚህም ሌላ፣ ከፕሮጀክት አስተዳደር ተቋም የፕሮጀክት አስተዳደር ባለሙያ የብቃት የምስክር ወረቀት አላቸው።

ጄምስ ባይሩሀንጋ/James Byaruhanga

ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ ዑጋንዳ

ጄምስ/James በአይቲ ኢዱስትሪ ውስጥ ከ20 አመታት በላይ የስራ ልምድ ያላቸው ሲሆን በተለያዩ መሪ የቴሌኮም ኩባንያዎች እና የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢዎች ውስጥ በስራ አስኪያጅነት ሰርተዋል። ጄምስ/James የRaxio ዑጋንዳን የእለት ከዕለት የስራና የንግድ ስራ እንቅስቃሴዎችን ከመቆጣጠር በተጨማሪ ከፍተኛ የጥራት ደረጃ ያለው አገልግሎት መቅረቡን ለማረጋገጥ ከደንበኞች ጋር በቅርበት ይሰራሉ።

ጄምስ/James ስለ ዑጋንዳ የገበያ ሁኔታዎች እና መጠነ ሰፊ የድርጅት ኔትወርክና የቴልኮ ግንኙነቶች ላይ የካበተ ሙያዊ ልምድ እና እውቀት አላቸው።

ጄምስ/James ቀደም ሲል በአማራጭ የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢነት በመሪነት ጥግ ላይ በሚገኘው በRoke Telkom ውስጥ ዋና አስተዳዳሪነትን፣ ዋና የአሰራር ኦፊሰርነት እና ዋና የቴክኖሎጂ ኦፊሰርነትን ጨምሮ በተለያዩ የስራ መደቦች ላይ አገልግለዋል። ጄምስ/James በዑጋንዳም ሆነ ኬንያ፣ ሩዋንዳ፣ ዛምቢያ እና ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክን በመሳሰሉ አጎራባች አገራት ለRoke የስራ እንቅስቃሴዎች የኩባንያው የቴክኒክ መሰረተ ልማትና የእቅድ ዝግጅት ኃላፊነት ተሰጥቷቸው ነበር።

ጄምስ/James ከRoke የስራ ድርሻ ቀደም ብሎ በMTN Uganda በተለያዩ የቴክኒክ ማማከር የስራ ድርሻዎች ለ5 አመታት እና በዑጋንዳና ጋና Africa Online ውስጥ ለ3 አመታት አገልግለዋል።

በእውቀት ታፈረ / Bewket Taffere

የራክሲዮ/ Raxio ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስኪያጅ

በዕውቀት የራክሲዮ ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሲሆኑ የተቋሙን ስትራቴጂዎች ተፈጻሚ የማድረግ እና የዕለት ተዕለት ተግባራቱን የማስተዳደር ኃላፊነት አለባቸው።

በዕውቀት በቴሌኮም፣ በመረጃ ቴክኖሎጂ (IT) እና በፊንቴክ(FINTECH) ከ19 ዓመት በላይ የሆነ የአመራር እና የኢንዱስትሪ የስራ ልምድ አላቸው። ስራ  የጀመሩት በኢትዮ ቴሌኮም ሲሆን በተቋሙ  የፕሮዳክት እና  እና ሰርቪስ ሥራ አስኪያጅ በመሆን አገልግለዋል፣ ከዚያ በኋላ በ CIT ኮሙኒኬሽን በሽያጭ ዳይሬክተርነት፣ በኢብር ሞባይል ፋይናንሻል ሰርቪስ (Ebirr MFS) ውስጥ በቺፍ ኦፕሬሽን ኦፊሰርነት (COO) እንዲሁም  በቻናል ቫስ/ ChannelVAS  ውስጥ በካንትሪ ማናጀርነት አገልግለዋል። በዕውቀት በራክሲዮ ያለንን ተልዕኮ ለማገዝ በቴክኖሎጂ፣ በንግድ ስራ ልማት እና በስራ አስተዳደር የካበተ ልምድ ይዘውልን መጥተዋል።

በቴሌኮሙኒኬሽን እና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የድህረ ምረቃ ተቋም MBA እንዲሁም ከጅማ ዩኒቨርስቲ በቢዝነስ ማኔጅመንት BA ድግሪ አላቸው።

ያኒክ ሱካኩሙ/Yannick Sukakumu

ዋና ሥራ አስያጅ፣ ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፑብሊክ/DRC

ያኒክ/Yannick የRaxio DRC ዋና ሥራ አስኪያጅ ሲሆኑ በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ ውስጥ የRaxioን አገልግሎት መስጫዎች የማልማትና አሰራራቸውን የማስተዳደር ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል። ያኒክ/Yannick በቴሌኮሞች፣ የቴኖሎጂና የፋይናንስ ኢንዱስትሪዎች ዘርፎች የ12 ዓመታት የፋይናንስና ስትራቴጂ የስራ ልምድ አዳብረዋል።

ያኒክ/Yannick ወደ Raxio ከመምጣታቸው በፊት  በGroup Vivendi Africa የEastern DRC ክፍለ አህጉራዊ ዳይሬክተር ሆነው አገልግለዋል። ከዚህ ቀደም ብሎም በBboxx Capital የGoma የኦፕሬሽኖች ዳይሬክተር ሆነው ሰርተዋል። ያኒክ/Yannick በተጨማሪም በBharti Airtel DRC በተለያዩ የፋይናንስ፣ የንግድና የስትራቴጂ የስራ ድርሻዎች ላይ ሰርተዋል።

ያኒክ/Yannick ከኮንጎ Universitie Protestante በኢኮኖሚክስ የመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቁ ሲሆን ቀጥለውም ከፍራንክፈርት የንግድ ስራና አስተዳደር ትምህርት ቤት/ Frankfurt School of Business and Management በማይክሮፋይናንስ ሁለተኛ ዲግሪ/ማስተርስ ዲግሪ/ አግኝተዋል።

Raphael Konan

የRaxio Ivory Coast ዋና ሥራ አስኪያጅ

Raphael በIvory Coast ውስጥ በሚገኘው የRaxio እህት ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ ነው። በዚያ ሐገር ውስጥ ለሚከናወኑት የቡድኑ ስራዎች ሰትራቴጂያዊ እቅድን፣ የሥራ አስተዳደርን የማስፈጸም እና የማስፋፋት ኃላፊነት አለበት።

AFRIPA Telecom, Côte d’Ivoire Telecom, Alink Telecom, Atlantic Group, PCCW Global, IHS እና በጣም በቅርቡ ደግሞ VIPNETን ጨምሮ በበርካታ የስራ መደቦች በሠራባቸው ድርጅቶች ውስጥ (በሐገር ውስጥ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ) የሞባይል ኔትወርክ ኦፕሬተሮችን እና የመሠረተ ልማት አገልግሎት አቅራቢዎችን (mobile network operators and infrastructure service providers) ስትራቴጂያዊ ክፍሎች በማስተዳደር ከ20 ዓመት የበለጠ የካበተ የስራ ልምድ አለው።

ከEcole de Commerce d’Abidjan (ESCA) በማናጅመንት፣ ከNational Polytechnic Institute Félix Houphouët-Boigny (INP-BHRaphael) በኢኮኖሚክስ እና በማርኬቲንግ ማናጅመንት ተመርቋል።

ባቪክ ፓትኒ/Bhavik Pattni

የራክሲዮ ግሩፕ

ባቪክ/Bhavik የራክሲዮ ግሩፕ/ Raxio Group ዋና የሰራተኞች ኃላፊ ሲሆኑ የኩባንያውን ስትራቴጂ በማዘጋጀትና የሰትራቴጂውን በንግድ ስራው ውስጥ በሙሉ መተግበር በማስተዳደር ረገድ ለዋና ስራ አስፈጻሚ ኦፊሰሩ/ CEO ድጋፍ የማድረግ ኃላፊነት አላቸው።

ቀደም ሲል ባቪክ/Bhavik አፍሪካ ላይ አተኩሮ የሚሰራው የራክሲዮ/Raxioን ልማት የሚመራው የአረንጓዴ መስክ የኢንቨስትመንት ድርጅት የሆነው የRoha Group የኢንቨስትመንት ተባባሪ ነበሩ። ባቪክ/Bhavik በRoha ከሀሳቡ መጸነስ ጀምሮ በራክሲዮ/ Raxio ግንባታ ውስጥ ተሳታፊ የነበሩ ሲሆን ለኢንቨስትመንት ትንተና፣ ስትራቴጂ፣ የገንዘብ ማሰባሰቢያ፣ አዲስ የገበያ እድገትና ምህንድስና ድጋፍ አድርገዋል። ከራክሲዮ/ Raxio በተጨማሪ ባቪክ/Bhavik ቀደም ሲል በማኑፋክቸሪንግ እና የጤና እንክብካቤ መስክ ለኩባኒያዎች የኢንቨስትመንት ትንታኔና ልማት ድጋፍ ሲያደርጉ ቆይተዋል። ከRoha ቀደም ብሎ ባቪክ/Bhavik የምስራቅ አፍሪካ የግል የኢኩዊቲ ድርጅት የሆነው የAscent የኢንቨስትመንት ተንታኝ ሆነው አገልግለዋል።

ባቪክ/Bhavik በሜካኒካል ምህንድስና ከኖቲንጋም ዩኒቨርሲቲ የBEng ዲግሪ አግኝተዋል።

ኬን ሀሪስ/Ken Harris

የፕሮጀክቶች ኃላፊ

ኬን/Ken የRaxio Group የፕሮጀክቶች ኃላፊ ሲሆኑ በመላው አፍሪካ አዳዲስ አገልግሎት መስጫዎችን ለማቋቋም የስምሪት እና የስጋት ጥናት ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል። ኬን/Ken ከአካባቢ ባለስልጣናት እና ባለቤቶች ጋር ግንኙነት በመፍጠር የስትራቴጂያዊ ቦታዎች ግዢን የሚያስተዳድሩ ከመሆኑም በተጨማሪ የእያንዳንዱን አገልግሎት መስጫ አርክቴክቶችና ተቋራጮች ምርጫና የግዢ ሂደት ይመራሉ። ኬን/Ken በእያንዳንዱ ፕሮጀክት የቆይታ ዘመን ውስጥ የRaxioን የፕሮጀክት እቅዶች፣ የጊዜ ሰሌዳዎችና በጀቶች ያስተዳድራሉ።

ኬን/Ken ቀደም ሲል በSchneider Australia ውስጥ የሰሩ ሲሆን በአንዳንድ የአለም መሪ የዳታ ማዕከል ተሳታፊዎች የተለያዩ የኤሌክትሪክ ፕሮጀክቶችን አስተዳድረዋል። ኬን/Ken የስራ ልምዳቸውን ያገኙት ካለፉት የ15 አመታት በላይ የትላልቅ ፕሮጀክቶች የቆይታ ዘመን ልማት፣ በመላው አፍሪካና አውሮፓ ከሞባይል ኢንዱስትሪ አረንጓዴ ልማትና ማስፋፊያ ስራቸው ነው።

ኬን/Ken በቴሌኮሙኒኬሽንስ እና ማርኬቲንግ ዲፕሎማ ያላቸው ከመሆኑም በተጨማሪ የከፍተኛ ፕሮጀክት አስተዳደር የምስክር ወረቀቶችን አግኝተዋል።

አሊ ማልሂ/Ali Malhi

የፋይናንስ ምክትል ፕሬዝዳንት/VP

አሊ/Ali ከRoha Group የፋይንስ ስራ አስኪያጅነት በሽግግር የመጡ የRaxio Group የፋይናንስ ምክትል ፕሬዝዳንት ናቸcው። አሊ/Ali የኮርፖሬት ፋይናንስን፣ የኢንቬስተር ግንኙነቶችና ሌሎችንም ጨምሮ የRaxio Groupን የዕለት ከእለት የፋይናንስ ግብይት ስራዎችነን ይቆጣጠራሉ።

አሊ/Ali በRoha Group ውስጥ ቀደም ሲል በነበራቸው የስራ ድርሻ የቡድኑን፣ ተቀጽላዎቹን እና የድርጅቱን የኢንቨስትመንት ፈንድ ፋይናንሶች አስተዳድረዋል። በተመሳሳይ ቀደም ሲል የImperial Logisticsን የፋይናንስ ስራ ያስተዳደሩ እንደመሆኑ በFMCG እና F&B ዘርፎች ስር በተለያዩ ብሄራዊ ኩባንያዎች የፋይናንስ ስራ ከ13 አመታት በላይ የስራ ልምድ አግኝተዋል።

አሊ/Ali ከግሪፍዝ ዩኒቨርሲቲ/Griffith University በMBA የተመረቁ ከመሆኑም በተጨማሪ ከሲፒኤ አውስትራሊያ/CPA እውቅና አግኝተዋል።

ማይንዛ ሙኖ/Mainza Moono

ስትራቴጂክ ዲቨሎፕመንት አሶሼት

ማይንዛ/Mainza በራክሲዮ ግሩፕ/Raxio Group ውስጥ የስትራቴጂክ ዲቨሎፕመንት አሶሼት ናቸው። ወደፊት ከፍተኛ ተስፋ ያለባቸውን ገበያዎች ለማጥናት በሚደረግ ጥረት በማገዝ ረገድ ከፍተኛ ሚና በመጫወት የቡድኑን አሻራ በመላው አፍሪካ  ማሳደግ እና ማስፋፋትን ይደግፋሉ።

የራክሲዮ ግሩፕን/Raxio Group ከመቀላቀላቸው ቀደም ብሎ፣ ማይንዛ/Mainza በሞሪሺየስ በሚገኘው የአፍሪካ ሊደርሺፕ ዩኒቨርሲቲ/African Leadership University ውስጥ የዕድገትና ስትራተጂ አሶሼት በመሆን ያገለገሉ ሲሆን፣ በድርጅት የካፒታል አቅም አሳዳጊ ቡድን ውስጥ ሰርተዋል። ከዚህ በፊት ደግሞ፣ በካሊፎርኒያ ሜንሎ ፓርክ በሚገኘው ማኬና ካፒታል ማኔጅመንት/ Makena Capital Management በንብረት ምደባ ቡድን ውስት የኢንቨስትመንት አናሊስት ሆነው ሰርተዋል።

ማይንዛ/ Mainza ከኦሃዮ ዌስኔያን ዩኒቨርሲቲ/ Ohio Wesleyan University በኢኮኖሚክስ የ BA ዲግሪ (በማዕረግ)  አላቸው። ከዚህም ሌላ፣ ከበደቡብ አፍሪካ ከሚገኘው የአፍሪካ ሊደርሺፕ አካዳሚም/ African Leadership Academy ተመራቂ ናቸው።

ኤክስፐርቶቻችን/ሙያተኞቻችንን ያናግሩ

ስለ አገልግሎቶቻችን እና የራሲዮ የዳታ ማዕከላት/Raxio Data Centres እንዴት ለንግድ ስራዎ ድጋፍ ሊያደርጉልዎ እንደሚችሉ በተመለከተ የበለጠ ማወቅ ይፈልጋሉ? ለጥያቄዎችዎ በደስተኝነት መልስ ለመስጠት ዝግጁ ነን። ቅጾቹን ይሙሉ እና በተቻለ ፍጥነት እናገኝዎታለን።