የዑጋንዳ የመጀመሪያው የድርጅት ደረጃ ያገኘ የዳታ ማዕከል

Raxio ዑጋንዳ የመጀመሪያው የድርጅት ደረጃ ያገኘ የተረጋገጠ የTier III ኒውትራል አስተላላፊ የዳታ ማዕከል ነው። በናማንቭ የኢንዱስትሪ ማዕከል እምብርት የሚገኘው Raxio ዑጋንዳ ከዋና ዋና የፋይበር መስመሮች ትይዩ በሚገኝ ተመራጭ ቦታ ላይ የሚገኝ ሆኖ ደረጃውን የጠበቀ የቦታ ለቦታ ግንኙነት፣ ወሰን ተሻጋሪ ግንኙነት፣ የፋይበርና አይቲ መሰረተ ልማት አገልግሎቶች ያቀርባል።

መገኛ ቦታ

ናማንቭ የኢንዱስትሪ ፓርክ
በካምፓላ ዳርቻ
ከዋና የፋይበር መስመር ትይዩ

ግንኙነት

የTier III ደረጃ
እስከ 400 ራኮች
በራክ ከ2 – 21 kW

ኢንዱስትሪዎች

ድርጅት
የፋይናንስ
ቴልኮሞች
ሚዲያ

በእጅጉ ውስብስብና ልዩ የአይቲና የቁጥጥር ችግሮች ለሚያጋጥሟቸው ኢንዱስትሪዎች ድጋፍ ለማድረግ እንሰራለን። ለእነዚህ ኢንዱስትሪዎች የንግድ ስራዎቻቸውን ለማሸጋገር የሚያስፈልጓቸውን የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶች በማቅረብ የዳታ ማዕከሎቻችን በመላው አፍሪካ የኢኮኖሚ እድገት፣ ማህበራዊ ልማት እና የዲጂታል ሽግግር አንቀሳቃሽነትን ያግዛሉ።

የግንኙነት አገልግሎቶች

በዑጋንዳ ካለው የዳታ አጠቃቀምና የመረጃ ቋት እድገት እና የንግድ ድርጅቶች የብሮድባንድ ዲጂታል ሽግግር ጋር ተያይዞ የRaxio የዳታ ማዕከል ለዑጋንዳ ኢኮኖሚ እድገት እና የዲጂታል ሽግግር እና ለMoICT የዳታ ስትራቴጂ ግቦች ድጋፍ የሚያደርግ የመሰረተ ልማት ማዕከል ሆኖ ያገለግላል።

የቦታ ለቦታ ግንኙነት

ስለ እኛ

ኒውትራል አስተላላፊ የዳታ ማዕከላችን አላማ ተኮር ሆኖ የተገነባ እና የተረጋገጠ የTier III ደረጃዎች ያሉት እንዲሁም 99.99% የአየር ሰዐት እና ተመራጭ ደረጃ ያለው መሳሪያ የሚያቀርብ ማዕከል ነው።

ማዕከሎቻችን ሁሉንም ለተልዕኮ ወሳኝ የአይቲ መሰረተ ልማቶች በቀን ለ24 ሰዐት/በሳምንት ለ7 ቀናት ያለ ምንም መቆራረጥ ለማስተናገድ እንዲቻል ለደንበኞች ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸው፣ እርስ በርሳቸው የተገናኙ ቦታዎችን ያቀርባሉ እንዲሁም እስከ 400 ራኮች የሚያስተናግዱ ቦታዎችን ያቀርባሉ።

ኒውትራል አስተላላፊ

ደንበኞችን ከተለያዩ አስተላላፊዎች ጋር እንዲገናኙ እና ከአስተላላፊዎች መካከል እንዲመርጡ ያስችላቸዋል።

የTier III ደረጃዎች

በቀን ለ24 ሰአት/በሳምንት ለ7 ቀናት ያልተቆራረጠ አገልግሎትን ለማረጋገጥ ያለ ምንም የመቆራረጫ ቦታ ተከታታይና ያልተቆራረጠ አገልግሎት ያቀርባሉ።

ተገጣጣሚ

በአገልግሎት መስጫው ውስጥ ፍላጎቶች በሚጠይቁት መሰረት እያደገ ከሚሄድ አቅም ጋር ወቅታዊና የወደፊት የደንበኞች ፍላጎቶችን ለማሟላት የተዘጋጁ ባለ ፌዝ አቅም ጥቅል መስመሮች።

PUE

1.3 የዲዛይን PUE ረሺዮ

ማቀዝቀዣ

ሀይል ቆጣቢ የአስተላላፊ መያዣ ያለው በተዘዋዋሪ ሙቀት እንዳይጨምር የሚያደርግ የማቀዝቀዣ ቴክኖሎጂ።

የሀይል ስርጭት

በባስባሮች ሀይል በሚያገኙ ተያያዥ ተሰቃይ መስመሮች አማካኝነት የሚደረግ የሀይል ስርጭት

የሀይል ዴንሲቲ

በአንድ ራክ ከ1 kW እስከ 21 kW ራኮችን የማስተናገድ አቅም ያለው

ራኮች

እስከ 58U. ተስማሚ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን የሚያቀርቡ መደበኛ 600 x 1200 ሚሜ ራኮች

ቁጥጥር

ከፍተኛ አፈጻጸምን ለማረጋገጥ እና ብልሽቶችን ፈልጎ ለማግኘት በቀን ለ24 ሰዐት/በሳምንት ለ7 ቀናት የሚደረግ

ደህንነት

የሳይት ላይ ደህንነትን ለማረጋገጥ በቀን ለ24 ሰዐት/በሳምንት ለ7 ቀናት የሚደረግ የCCTV ቁጥጥር። በመግቢያና ሰርቨሮች መካከል እስከ 7 ዙሮች የሚሰራ አካላዊ ደህንነት።

ታሪካችን

የRaxio የዳታ ማዕከል የድርጅት ደረጃ ያለው የዳታ ማዕከል ሲሆን በናማንቭ፣ ዑጋንዳ በቅርቡ ስራ ይጀምራል።

Raxio በዑጋንዳ የመጀመሪያውን ድርጅት እና የአስተላላፊ ደረጃ ያለው የዳታ ማዕከል አገልግሎት መስጫን ያንቀሳቅሳል። Raxio የተመሰረተው በ2018 ዓ.ም በመላው ምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ የዲጂታል ኢኮኖሚ መሰረት ለመጣል የተቋቋመው የRoha Group ኩባንያ በሆነው በFirst Brick Holdings (“FBH”) ነው። Roha በመላው አፍሪካ አዳዲስ የንግድ ድርጅቶችን የሚገነባና የሚያቋቁም የUS Greenfield የኢንቨስትመንት ኩባንያ ነው።

የዑጋንዳ ኢኮኖሚ የዲጂታል ሽግግር በፍጥነት እያደገ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የዳታ ማዕከሉ የሚገነባው ይህን ሸግግግር የሚደግፍ ዳታ በዳታ ቋት መቀመጥና 100% ያክሉን ጊዜ በትክክል መገኘትና ጥቅም ላይ መዋል በሚችልበት መልኩ ለመጠነ ሰፊና እያደጉ የመጡ የአገልግሎት መስጫዎች ፍላጎቶችን ለማሟላት ነው። የዳታ ማዕከሉ በ2021 ዓ.ም ሲከፈት በኒውትራል አስተላላፊነት የሚሰራና በሙሉ አቅሙ መስራት ሲጀምር እስከ 400 ራኮችን የማስተናገድ አቅም ያለው በዑጋንዳ በአይነቱ የመጀመሪያ፣ ብቸኛ የTier III ማረጋገጫ ያለው የአገልግሎት መስጫ ሆኖ ያገለግላል።

ተጨማሪ መረጃ ያግኙ

Raxio ለፋይናንስ አገልግሎቶች፣ የመንግስትና ከአነስተኛ እስከ መካከለኛ ድርጅቶች (SMEs) የዳታ ቋት፣ የንግድ ስራ ቀጣይነትና የአደጋ ፍላጎቶቻቸውን በማሟላት አዳዲስ እድሎችን ይከፍትላቸዋል።

ጄምስ ባሩሀንጋ/James Byaruhanga

ዋና ስራ አስኪያጅ

ከእነ ማን ጋር አብረን እንደምንሰራ

Raxio ለአገልግሎት መስጫዎቹ የዲዛይንና ግንባታ ስራ ከዩኬ Future-techን፣ እና ከዑጋንዳ Symbion of Ugandaን ተመራጭ ደረጃ ያላቸው የንግድ አጋሮቹ አድርጎ ከመምረጡም በተጨማሪ ስራ ሲጀምርም ከፍተኛ አቅሙን ተጠቅሞ ለመስራትና የስራ እንቅስቃሴውን ለማካሄድ ጠንካራና ልምድ ያለው የአስተዳደር ቡድን አቋቁሟል።

የኢንቨስትመንት አጋሮች

የቴክኒክ አጋሮች

ጄምስ ባሩሀንጋ/James Byaruhanga

ዋና ሥራ አስኪያጅ

ጄምስ/James በአይቲ ኢዱስትሪ ውስጥ ከ20 አመታት በላይ የስራ ልምድ ያላቸው ሲሆን በተለያዩ መሪ የቴሌኮም ኩባንያዎች እና የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢዎች ውስጥ በስራ አስኪያጅነት ሰርተዋል። ጄምስ/James የRaxio ዑጋንዳን የእለት ከዕለት የስራና የንግድ ስራ እንቅስቃሴዎችን ከመቆጣጠር በተጨማሪ ከፍተኛ የጥራት ደረጃ ያለው አገልግሎት መቅረቡን ለማረጋገጥ ከደንበኞች ጋር በቅርበት ይሰራሉ።

ጄምስ/James ስለ ዑጋንዳ የገበያ ሁኔታዎች እና መጠነ ሰፊ የድርጅት ኔትወርክና የቴልኮ ግንኙነቶች ላይ የካበተ ሙያዊ ልምድ እና እውቀት አላቸው።

ጄምስ/James ቀደም ሲል በአማራጭ የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢነት በመሪነት ጥግ ላይ በሚገኘው በRoke Telkom ውስጥ ዋና አስተዳዳሪነትን፣ ዋና የአሰራር ኦፊሰርነት እና ዋና የቴክኖሎጂ ኦፊሰርነትን ጨምሮ በተለያዩ የስራ መደቦች ላይ አገልግለዋል። ጄምስ/James በዑጋንዳም ሆነ ኬንያ፣ ሩዋንዳ፣ ዛምቢያ እና ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክን በመሳሰሉ አጎራባች አገራት ለRoke የስራ እንቅስቃሴዎች የኩባንያው የቴክኒክ መሰረተ ልማትና የእቅድ ዝግጅት ኃላፊነት ተሰጥቷቸው ነበር።

ጄምስ/James ከRoke የስራ ድርሻ ቀደም ብሎ በMTN Uganda በተለያዩ የቴክኒክ ማማከር የስራ ድርሻዎች ለ5 አመታት እና በዑጋንዳና ጋና Africa Online ውስጥ ለ3 አመታት አገልግለዋል።

አዳዲስ ዜናዎች

ኤክስፐርቶቻችን/ሙያተኞቻችንን ያናግሩ

የRaxio የዳታ ማዕከል፣ ፕሎት 781፣ ህንጻ 113፣ ናማንቭ የኢንዱስትሪ ፓርክ፣ ሙኮኖ፣ ካምፓላ

ስለ አገልግሎቶቻችን እና የራሲዮ የዳታ ማዕከላት/Raxio Data Centres እንዴት ለንግድ ስራዎ ድጋፍ ሊያደርጉልዎ እንደሚችሉ በተመለከተ የበለጠ ማወቅ ይፈልጋሉ? ለጥያቄዎችዎ በደስተኝነት መልስ ለመስጠት ዝግጁ ነን። ቅጾቹን ይሙሉ እና በተቻለ ፍጥነት እናገኝዎታለን።