የአፍሪካ እርስ በርስ የተገናኘ የዲጂታል ሲስተም
በዳታ ማዕከል ኢንዱስትሪ ውስጥ መሪ እንደመሆናችን ከአፍሪካ አንዳንድ በፈጠራ ላይ ከተመሰረቱ ኩባንያዎች ጋር በንግድ ስራቸው ላይ በሙሉ የዲጂታል ሽግግሮቻቸውን እንደሚመሩ ለመርዳት በተለያዩ ዘርፎች ላይ አብረን እንሰራለን።
ከፋይናንስ አገልግሎት ተቋማት አንስቶ እስከ ሚዲያ ተቋማት ድረስ የውስጥ ኤክስፐርቶቻችን ምንም ሁለት የንግድ ድርጅቶች የተለያዩ እንዳልሆኑ እና እያንዳንዱ ኢንዱስትሪ የራሱ የተለያዩ ተግዳሮቶችና እድሎች እንደሚያጋጥማቸው ይገነዘባሉ። በአካባቢ ገበያ እውቀታችን እና የአይቲ ሙያዊ ልምዳችን ታግዘን ልዩ የኢንዱስትሪ ፍላጎቶችዎን የሚያሟሉ ተያያዥ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ለማዘጋጀት ከእርስዎ ጋር አብረን መስራት እንችላለን።
የፋይናንስ አገልግሎቶች
የዳታ ማዕከሎቻችን ለአፍሪካ እጅግ ግዙፍ የባንክ፣ ኢንሹራንስ እና የካፒታል ገበያዎች ድርጅቶች ለተልዕኮ ወሳኝ የዲጂታል ንብረቶች ጥበቃ ከማድረግ በተጨማሪ እርስ በርሳቸው እንዲገናኙ ያደርጋሉ። እያደገ በመጣ ውስብስብነት፣ ከፍተኛ የደንብ እና ጥብቅ የሸማች የሚጠበቁ ሁኔታዎች የአፍሪካ የፋይናንስ ማህበረሰብ የአይቲ ሲስተሞቻቸውን እነዚህን ደረጃዎች በሚያሟላ መልኩ ማሻሻል ይኖርባቸዋል።
ሙሉ በሙሉ ህግን ባከበረ አኳኋን አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ፍጥነት፣ ደህንነትና አስተማማኝነት በማቅረብ ተቋማቱን የመጀመሪያና የአደጋ ማገገሚያ ፍላጎቶቻቸውን እንዲያሟሉ ከመርዳት ባሻገር ከፍተኛ፣ እጅግ ወጪ ቆጣቢ ደረጃዎችን የተከተለ የዳታ ማዕከል አስተዳደር እናቀርባለን።
የይዘት አቅርቦት ኔትወርኮች (CDNs)
CDNዎች በአፍሪካ የኢንተርኔት ተደራሽትን የበለጠ ተደራሽና ተመጣጣኝ ዋጋ ያለው እንዲሆን የሚያደርጉ መስመሮች ናቸው። ሸማቾች የራሳቸውን የማገናኛ ሰርቨሮች በማገናኘት ያለ ምንም መቆራረጥ የአካባቢያቸውን የኢንተርኔትት ይዘት ማግኘት ይችላሉ። ይህ ውድ የአህጉራዊና ከባህር በታች ግንኙነት ወጪን በማስቀረት የኢንተርኔት ይዘትን ርካሽና ፈጣን ለማድረግ ያስችላል።
የዳታ ማእከሎቻችን CDNኖች የማገናኛ አገልግሎቶችን ከቦታ ቦታ ለማገናኘት የሚጠይቁትን የአየር ሰአትና የቦታ ላይ መሰረተ ልማት ደረጃ ከማቅረባቸውም በተጨማሪ ወጪ ቆጣቢ፣ ድብቅነታቸው ዝቅተኛ የሆኑ የአካባቢ የኢንተርኔት ይዘቶችን ያቀርባሉ።
የክላውድ አገልግሎት አቅራቢዎች
የክላውድ ኒውትራል የዳታ ማዕከሎቻችን የክላውድ አገልግሎት አቅራቢዎች የ“ጥግ” አቀማመጥን ማለትም ከህዝብ ክላውድ ይልቅ ለተጠቃሚ ቅርብ የሆኑ አቀማመጦችን በመጠቀም ለደንበኞቻቸው የተለያዩ አገልግሎቶችን የሚያቀርቡበት የተረጋጋ ቦታ ያቀርባሉ። ይህ በተለይም በድብቅነት ላይ ለተመሰረቱ መተግበሪያዎች አስፈላጊ ከመሆኑም በተጨማሪ ለተጠቃሚዎች የአእምሮ እረፍት ለመፍጠርና መረጃው በዋናነት ከየት እንደሚስተናገድ በተመለከተ እውቀት እንዲያገኙ ለማድረግ ጠቃሚ ነው።
የክላውድ አገልግሎቶቻችን አጋሮች በዳታ ማዕከሎቻችን ለሚስተናገዱ የክላውድ ፕላትፎርሞች አስተማማኝ ግንኙነቶችን ለመገንባት ከግንኙነት አጋሮቻችን ጋር በጋራ ይሰራሉ። በክላውድ አጋሮቻችን የሚቀርቡት አገልግሎቶች የሚከተሉት ናቸው፡
- የመሰረተ ልማት አገልግሎት
- የሶፍትዌር አገልግሎት
- የአደጋ ማገገሚያ አገልግሎት
- የፕላትፎርም አገልግሎት
ድርጅት
ለመስራት ዳታ በማግኘት ላይ የተመሰረቱ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው SMEዎች መኖር ጋር ተያይዞ አገልግሎቶች ሳይቆራረጡ ቅልጥፍናንና ተቀያያሪነትን ይዞ የመቀጠል ፍላጎት ወሳኝ ነው። ስኬታማነት እንደ የሂሳብ አያያዝ ፕላትፎርሞች፣ የERP ሲስተሞች፣ የHRM ሲስተሞች፣ የመልዕክት ሲስተሞች፣ የፋይል ሰርቨሮችና ሌሎችንም የመሳሰሉ ወሳኝ የንግድ ስራ አሰራሮችን ውጤታማና አውቶማቲክ በማድረግ ላይ በእጅጉ የተመሰረተ ነው።
የዳታ ማዕከል አገልግሎቶቻችን ድርጅቶችን እና SMEዎችን የንግድ ስራቸውን ቀጣይነት እና የአደጋ መቋቋሚያ እቅድ ዝግጅቶቻቸውን እንዲያሻሽሉ ያስችሏቸዋል። የጋራ መሰረተ ልማቶችን ተለዋዋጭነትና ደህንነትን ከፍ በሚያደርግ መልኩ በመዘርጋት ከፍተኛ የኢኮኖሚ ስኬልን እንዲያሳኩ እንረዳዎታለን።
ኔትወርክና ግንኙነት
የቴሌኮሙኒኬሽን ኩባንያዎች እንደ የፋይበር ኦፕቲክ ኔትወርኮች፣ የሞባይል ማማ ኔትወርኮች ወይም የሞባይል ገንዘብ ኔትወርኮች ባሉት የዲጂታል አገልግሎቶችና መሰረተ ልማቶች ላይ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት እያደረጉ ቢሆንም ጠንካራ የአደጋ መቋቋሚያ አቅሞች ያስፈልጓቸዋል። የዳታ ማዕከሎቻችን የተልዕኮ ወሳኝ ሲስተሞች ተሸካሚዎች ከዋና ማስተላለፊያ ማእከላት በአመቺ ርቀት ላይ እንዲገኙ ያስችላሉ።
በተጨማሪም የMeet Me ክፍሎቻችን ለISPዎች እና CDNኖች የግንኙነት ኒውትራል የመገናኛ ቦታዎች ሆነው የሚያገለግሉ ከመሆኑ ጎን ለጎን መጠነ ሰፊ የግንኙነት ኔትወርክ አጋሮቻችን ተሸካሚዎች አገልግሎቶቻቸውን እንዲያሰፉ እና አዲስ የገቢ መስመሮች እንዲፈጥሩ ያስችላሉ።
ሚዲያ
የዲጂታል ሚዲያ ፕላትፎርሞች ቀስ በቀስ መደበኛ ሚዲያውን እየተኩ ከመምጣታቸው ጋር ተያይዞ የሚዲያው ምህዳር እየተቀየረ ነው። የሚዲያ ተቋማት በአሁኑ ወቅት ተወዳዳሪ ጥቅማቸው ወቅታዊ ይዘቶችን ለወደፊት ግልጋሎት በማህደር ይዘው በማስቀመጥ ችሎታቸው እና ጥያቄ ሲቀርብላቸው ቪዲዮ እና አሳታፊ አገልግሎቶችን በማቅረብ ችሎታቸው ላይ የተመሰረተ እንደሆነ ተገንዝበዋል። በዳታ ማዕከሎቻችን ስር መስተናገድ የሚዲያ ኩባንያዎችን ለተጠቃሚዎች ይዘት በማቅረብ እና የብሮድካስት ዳታ ይዞ የማቆየት የኢንዱስትሪ ደንብ ኃላፊነትን በተሟላ ሁኔታ በማሟላት ዝግጁ ይዘት ለማቅረብ ያስችሏቸዋል።