የቡድኑ አመራር ቡድን

ሮበርት ሙሊንስ/ Robert Mullins
ዋና ስራ አስፈጻሚ ኦፊሰር

ማርሊን ኪኒፎ-ዙኖን/Marlène Kiniffo-Zounon
ዋና የአሰራር ኦፊሰር

ማርኮ አንጀሊኖ/Marco Angelino/
ዋና የፋይናንስ ኦፊሰር

ሮበርት ሳውንደርስ/ Robert Saunders
ዋና የቴክኖሎጂ ኦፊሰር

ጁዲ ንጉሩ/Judy Nguru/
የስትራቴጂያዊ እቅድ ዝግጅት ከፍተኛ ምክትል ፕሬዝዳንት /VP/

ባቪክ ፓትኒ/ Bhavik Pattni
የንግድ ስራ አሰራሮች ምክትል ፕሬዝዳንት /VP/
የዳይሬክተሮች ቦርድ

በርናርድ ጂዮግህጋን/Bernard Geoghegan
ሊቀ መንበር /ሰብሳቢ/

Brooks Washington
Non-Executive Director

ፍራንስ ቫን ሼይክ/Frans Van Schaik
ስራ አስፈጻሚ ያልሆኑ ዳይሬክተር

ማርቪን ቤል/Marvin Bell
ስራ አስፈጻሚ ያልሆነ ዳይሬክተር

ፒየር ኢማኑኤል ቤሉሽ/ Pierre-Emmanuel Beluche
ስራ አስፈጻሚ ያልሆኑ ዳይሬክተር
የኩባንያ ስራዎች አስተዳደር ቡድን

ጄምስ ባያሩሀንጋ/James Byaruhanga
ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ ዑጋንዳ

በውቀት ታፈረ
ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ ኢትዮጵያ

ያኒክ ሱካኩሙ/Yannick Sukakumu
ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ /DRC/

ራፋኤል ኮናን/Raphael Konan
ዋና ሥራ አስኪያጅ

ሮበርት ሙሊንስ/ Robert Mullins
ዋና ስራ አስፈጻሚ ኦፊሰር
ሮበርት/Robert/ የራዚዮ ግሩፕ /Raxio Group/ ዋና ስራ አስፈጻሚ ኦፊሰር /CEO/ ናቸው። ግለሰቡ ለስትራቴጂያዊ እቅድ ዝግጅት፣ የራዚዮ/Raxio/ የዳታ ማዕከላት በመላው አፍሪካ መስፋፋትን የመምራት እንዲሁም ቡድኑ ከአለም አቀፍና ክፍለ አህጉራዊ ደንበኞችና አጋሮች ኔትወርክ ጋር የሚያደርገውን ግንኙነት የመምራት ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል። ሮበርት/Robert/ በተጨማሪም የሮሀ ግሩፕ/ Roha Group/ አጋር ናቸው።

ማርሊን ኪኒፎ-ዙኖን/Marlène Kiniffo-Zounon
ዋና የአሰራር ኦፊሰር
ማርሊን /Marlène/ የራዚዮ ቡድን/ Raxio Group/ ዋና የአሰራር ኦፊሰር ሲሆኑ ለቡድኑ አጠቃላይ የአሰራር ጉዳዮች፣ ለአለም አቀፍ ሽያጮችና የማርኬቲንግ ስራዎች ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል። ማርሊን /Marlène/ ወደ ራዚዮ/Raxio/ ከመቀላቀላቸው ቀደም ብሎ የHelios Towers የምዕራብና መካከለኛው አፍሪካ ክልል ዋና ስራ አስፈጻሚ ኦፊሰር /CEO/ ሆነው ያገለገሉ ከመሆኑም በተጨማሪ የመጀመሪያዋ ሴት የHelios Towers Group የከፍተኛ አመራር ቦርድ ቋሚ አባል ነበሩ።

ማርኮ አንጀሊኖ/Marco Angelino/
ዋና የፋይናንስ ኦፊሰር
ማርኮ/Marco/ የራዚዮ ቡድን /Raxio Group/ ዋና የፋይናንስ ኦፊሰር /CFO/ ናቸው። ግለሰቡ በኢነርጂ፣ መሰረተ ልማትና የባንክ ስራ የ15 ዓመት ልምድ አላቸው። ሙያዊ ልምዳቸው በበርካታ የተለያዩ የንብረት ምድቦች (ታዳሽ ሀይል፣ የክፍያ መንገዶች፣ የባቡር ትራንስፖርት) እና የተለያዩ ጂኦግራፊያዊ ቦታዎች (አፍሪካ፣ አውሮፓ፣ ዩኤስኤ፣ ኤልኤ) ስር አጠቃላይ የኢንቨስትመንት እሴት ሰንሰለት ፈጠራን ያጠቃልላል።

ሮበርት ሳውንደርስ/ Robert Saunders
ዋና የቴክኖሎጂ ኦፊሰር
ሮበርት /Robert/ የራዚዮ ቡድን /Raxio Group/ ዋና የቴክኖሎጂ ኦፊሰር /CTO./ ናቸው። ግለሰቡ ለራዚዮ /Raxio/ የዳታ ማዕከል አገልግሎት መስጫዎች ዲዛይን፣ ግንባታ፣ ሙከራና ሥራ ማስጀመር ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል። ሮበርት /Robert/ ከ17 ዓመታት በላይ የኢንዱስትሪ የሥራ ልምድ በመያዝ ለዲጂታል ትራንስፎርሜሽን/ ሽግግር ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ባለሙያ ናቸው።

ጁዲ ንጉሩ/Judy Nguru/
የስትራቴጂያዊ እቅድ ዝግጅት ከፍተኛ ምክትል ፕሬዝዳንት /VP/
ጁዲ/Judy/ የስትራቴጂያዊ እቅድ ዝግጅት ከፍተኛ ምክትል ፕሬዝዳንት /VP/ ሲሆኑ የራዚዮ ቡድን /Raxio Group/ የመስፋፋትና እድገት ስትራቴጂን የማስፈጸም ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል። ጁዲ/Judy/ በቴክኖሎጂ፣ ቴሌኮሙኒኬሽንስ፣ FMCG እና ፋይናንስ ከ16 ዓመታት በላይ የሥራ ጠንካራ ልምድ ያላቸው ባለሙያ ናቸው። i

ባቪክ ፓትኒ/ Bhavik Pattni
የንግድ ስራ አሰራሮች ምክትል ፕሬዝዳንት /VP/
ባቪክ /Bhavik/ የራዚዮ ቡድን /Raxio Group/ ዋና የሰራተኞች ኃላፊ ናቸው። ግለሰቡ የኩባንያውን ስትራቴጂ በማዘጋጀትና ትግበራውን በመቆጣጠር ላይ ለዋና ስራ አስፈጻሚ ኦፊሰሩ /CEO/ ድጋፍ የማድረግ ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል። ባቪክ /Bhavik/ ቀደም ሲል በRoha Group ውስጥ የኢንቨስትመንት ተባባሪ ነበሩ።

በርናርድ ጂዮግህጋን/Bernard Geoghegan
ሊቀ መንበር /ሰብሳቢ/
በርናርድ/Bernard/ የራዚዮ ቡድን /Raxio Group/ ሊቀ መንበር /ሰብሳቢ/ ሲሆኑ በተለያዩ የአማካሪነት የሥራ ድርሻዎች ላይ ይሰራሉ። ግለሰቡ በዳታ ማዕከል ኢንዱስትሪ ውስጥ የDigital Realty የMD እና SVP EMEA ኃላፊነትን፣ የColt Data Centre Services ስራ አስፈጻሚ VP እና የInterxion Ireland እና Interxion Deutschland ጊዜያዊ MD ሆኖ መስራትን ጨምሮ በተለያዩ የከፍተኛ ኃላፊነት የስራ መደቦች ላይ ሰርተዋል።

Brooks Washington
Non-Executive Director
Brooks is the Founder of Roha Group and serves as a board member on Roha Group’s portfolio companies. Before founding Roha in 2013, Brooks was a consultant at McKinsey & Company, where he co-founded the company’s office in Lagos. Brooks has also served as CEO of Juniper Glass Industries.

ፍራንስ ቫን ሼይክ/Frans Van Schaik
ስራ አስፈጻሚ ያልሆኑ ዳይሬክተር
ፍራንስ/Frans/ በራዚዮ ቡድን /Raxio Group/ ውስጥ ስራ አስፈጻሚ ያልሆኑ ዳይሬክተር ሲሆኑ የRoha አጋር እና የAfrican Asset Finance Company Inc ሊቀ መንበር /ሰብሳቢ/ እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኦፊሰር /CEO/ ናቸው። ፍራንስ/Frans/ ቀደም ሲል የTribute Capital መስራች ከመሆናቸውም በተጨማሪ የLogispring ተቆጣጣሪ አጋር፣ የGilde Investment Funds መለስተኛ አጋር፣ እና የተለያዩ የኢንዱስትሪ ቡድኖች ጊዜያዊ ዋና ስራ አስፈጻሚ ኦፊሰር /CEO/ ሆነው አገልግለዋል።

ማርቪን ቤል/Marvin Bell
ስራ አስፈጻሚ ያልሆነ ዳይሬክተር
ማርቪን /Marvin/ የMeridiam የኢንቨስትመንት ዳይሬክተር ሲሆኑ በአፍሪካ የፕሮጀክት ልማትና አፈጻጸም ላይ በትኩረት ይሰራሉ። ማርቪን /Marvin/ በኢትዮጵያ የቱሉ ሞዬ የጂኦተርማል ፕሮጀክትን እና የራዚዮ/Raxio/ የዳታ ማዕከል ፕላትፎርምን ያስተዳድራሉ። ማርቪን /Marvin/ ወደ Meridiam ከመቀላቀላቸው ቀደም ብሎ በለንደን የCDC Group የኢንቨስትመንት ሥራ አስኪያጅ ሆነው አገልግለዋል።

ፒየር ኢማኑኤል ቤሉሽ/ Pierre-Emmanuel Beluche
ስራ አስፈጻሚ ያልሆኑ ዳይሬክተር
ፒየር – ኢማኑኤል /Pierre-Emmanuel/ የMeridiam የኢንቨስትመንት ዳይሬክተር ሲሆኑ ለአፍሪካና አውሮፓ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል። ፒየር – ኢማኑኤል /Pierre-Emmanuel/ ወደ Meridiam ከመቀላቀላቸው ቀደም ብሎ ለ10 ዓመታት ያክል የፈረንሳይ ግምጃ ቤት ኃላፊ/ French Treasury/ ሆነው ያገለገሉ ሲሆን የልማት ፋይናንስን፣ የግዛት ብድር የፋይናንስ ድጋፍን እንዲሁም የኮርፖሬትና የፋይናንስ ደንብን የመቆጣጠር ኃላፊነት ነበራቸው። ፒየር – ኢማኑኤል /Pierre-Emmanuel/ በተጨማሪም የእሲያ ልማት ባንክ /Asian Development Bank/ የቦርድ አባል ሆነው ያገለገሉ ሲሆን የሙያ ስራቸውን የጀመሩት በBNP Paribas ነበር።

ጄምስ ባያሩሀንጋ/James Byaruhanga
ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ ዑጋንዳ
ጄምስ /James/ በአይቲ ኢንዱስትሪ ውስጥ ከ20 ዓመታት በላይ የስራ ልምድ ያላቸው ሲሆን የመሪ ቴሌኮሞች እና ISPs ስራ አስኪያጅ ሆነው አገልግለዋል። ጄምስ /James/ የራዚዮ ኡጋንዳ/ Raxio Uganda/ን የዕለት ከዕለት የንግድ ስራ እንቅስቃሴዎች የሚቆጣጠሩ ከመሆኑም በተጨማሪ ልዩ የአገልግሎት አቅርቦትን ለማረጋገጥ ከደንበኞች ጋር በቅርበት ይሰራሉ።

በውቀት ታፈረ
ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ ኢትዮጵያ
በውቀት የራዚዮ ኢትዮጵያ /Raxio Ethiopia/ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሲሆኑ የድርጅቱን ስትራቴጂ የማስፈጸም እና የአገልግሎት መስጫዎቹን የዕለት ከዕለት የሥራ እንቅስቃሴዎች የማስተዳደር ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል። በውቀት ከ19 ዓመታት በላይ የቴሌኮሞች፣ አይቲና ፊንቴክ የአመራርነት የሥራ ልምድ አላቸው።

ያኒክ ሱካኩሙ/Yannick Sukakumu
ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ /DRC/
ያኒክ /Yannick/ የRaxio DRC ዋና ሥራ አስኪያጅ ሲሆኑ በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ውስጥ የራዚዮ /Raxio/ አገልግሎት መስጫዎችን ልማትና የአሰራር አስተዳደር ስራዎች በኃላፊነት ይመራሉ። ያኒክ /Yannick/ በቴሌኮሞች፣ የቴክኖሎጂና የፋይናንስ ኢንዱስትሪዎች ውስጥ በፋይናንስና ስትራቴጂ ስራዎች ከ12 ዓመታት በላይ የሥራ ልምድ አላቸው።

ራፋኤል ኮናን/Raphael Konan
ዋና ሥራ አስኪያጅ
ራፋኤል /Raphael/ የራዚዮ /Raxio/ የአይቮሪኮስት ተቀጽላ ኩባንያ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሲሆኑ የስትራቴጂያዊ እቅድ አፈጻጸምን፣ የአሰራር አስተዳደርን እና በአገሪቱ የቡድኑ የስራ እንቅስቃሴዎች መስፋፋትን ይቆጣጠራሉ። ራፋኤል /Raphael/ በAFRIPA ቴሌኮም፣ የኮትዲቩዋር ቴሌኮም፣ Alink ቴሌኮም፣ Atlantic Group፣ PCCW Global፣ IHS እና በጣም በቅርቡ በVIPNET ውስጥ ስትራቴጂያዊ ክፍሎችን የማስተዳደር ከ20 ዓመታት በላይ የተከማቸ የሥራ ልምድ አላቸው።