ቦታዎች

የዳታ ማዕከላት በመላው አፍሪካ በማደግ ላይ ናቸው

የRaxio Group የዳታ ማዕከል አገልግሎት መስጫዎች በአሁኑ ወቅት በዑጋንዳ እና ኢትዮጵያ የሚገኙ ሲሆን ተጨማሪ ዋና መ/ቤቶች በዱባይ እና ኒውዮርክ ይገኛሉ። በመላው አፍሪካ የኢንተርኔት አጠቃቀም መጠን እያደገ መሄዱን ከመቀጠሉ ጋር ተያይዞ Raxio Group የአፍሪካ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ዋነኛ አንቀሳቃሽ የመሆን አላማ አለው።

ድርጅቶች በዚህ የዲጂታይዜሽን ደረጃ ልክ ዝግጁ እንዲሆኑ እና የደንበኞቻቸውን እያደገ የሚሄድ የግንኙነት እና የባንድ ስፋት ፍላጎቶች እንዲያሟሉ ለማስቻል በምንሰራው ስራ የአይቲ ሲስተሞች እድገት በድብቅ የዳታ ፍላጎት የተገደበባቸውን የአፍሪካ አገራት በመለየት የዳታ ማዕከሎቻችንን በመላው አህጉሪቱ በፍጥነት በማስፋፋት ይህን ፍላጎት ለማሟላት እንሰራለን።

ሳይቱን ይመልከቱ

ዑጋንዳ

Raxio ዑጋንዳ በካምፓላ ዳርቻ በሚገኘው የናማንቭ የኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ የሚገኝ የተረጋገጠ የTier III ኒውትራል ተሸካሚ የዳታ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ነው። ዑጋንዳ ውስጥ የብሮድባንድ አጠቃቀም መጠን እያደገ እና ደንቦች በሀገሪቱ ውስጥ የአደጋ መቋቋሚያ ጣቢያዎች መኖር እንዳለባቸው የሚደነግጉ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የአገር ውስጥ የቦታ ለቦታ ግንኙነት ያላቸው አገልግሎቶች እያደጉ ነው።

ከፋይበር መስመሮች ጋር በማገናኘት የተቋቋመው Raxio ዑጋንዳ የሚገኝበት ቦታ የደንበኞችን የመጀመሪያ ፍላጎቶችና የአደጋ መቋቋሚያ ደንቦችን ለማሟላት በሚያስችለው ተመራጭ ቦታ ላይ ነው። የኡጋንዳን የንግድ ድርጅቶች እየያደገ የመጣ የመረጃ ቋት፣ የቦታ ለቦታ ግንኙነት እና የክላውድ አገልግሎት መስፈርቶች ለማሟላት የሚያስችል ከፍተኛ አቅም ያቀርባል። Raxio ዑጋንዳ የደንበኛ ስምሪቶች በቀን ለ24 ሰአት/በሳምንት ለ7 ቀናት ከአስተማማኝ ደህንነት እና አለመቆራረጥ ጋር በከፍተኛ አቅማቸው የሚሰሩበትን ሁኔታ ለማረጋገጥ እስከ 400 ራኮችን ማስተናገድ እና እስከ 1.5MW የአይቲ ሀይል ማቅረብ ይችላሉ።

የዳታ ማዕከል

የRaxio የዳታ ማዕከል፣ ፕሎት 781፣ ህንጻ 113፣ ናማንቭ የኢንዱስትሪ ፓርክ፣ ሙኮኖ፣ ካምፓላ

ዋነና መስሪያ ቤት

የRaxio የዳታ ማዕከል፣ ፕሎት 781፣ ህንጻ 113፣ ናማንቭ የኢንዱስትሪ ፓርክ፣ ሙኮኖ፣ ካምፓላ

ሳይቱን ይመልከቱ

ኢትዮጵያ

Raxio ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ዳርቻ የሚገኝ የTier III ኒውትራል ተሸካሚ የዳታ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ነው። ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የአንዳንዶቹ የምስራቅ አፍሪካ ግዙፍ የሶፍትዌር ኩባንያዎች መገኛ በመሆኗ ከተለዋዋጭ የSME ኢኮሲስተም ተጠቃሚ ትሆናለች።

የቦታ ለቦታ ግንኙነት ፍላጎቶች በፍጥነት እያደጉ ከመሆኑና ወደ ቴሌ ኮሙኒኬሽን ምህዳር አዳዲስ ገቢዎች እየገቡ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የመጀመሪያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽ ደረጃ ላይ ደርሷል።

ከዋና የፋይበር መስመሮች ጋር በማገናኘት የተቋቋመው Raxio ኢትዮጵያ እያደገ የመጣውን የሀገር ውስጥ የክላውድ ግንኙነት እና የቦታ ለቦታ ግንኙነት አገልግሎቶችን ለማሟላት እያገለገለ ይገኛል። ማዕከሉ በመጀመሪያ ላይ አቅሙን በእጥፍ ከማሳደግ እምቅ አቅም ጋር እስከ 400 ራኮችን ማስተናገድ እና እስከ 1.5MW ማቅረብ ከመቻሉም በተጨማሪ በቀን ለ24 ሰአት/በሳምንት ለ7 ቀናት የማዕከል አገልግሎት ከአስተማማኝ ደህንነት እና አለመቆራረጥ ጋር ለተጠቃሚዎች ማቅረብ ይችላል።

የዳታ ማዕከል

የRaxio የዳታ ማዕከል፣ የአይሲቲ የኢንዱስትሪ ፓርክ፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

ዋና መስሪያ ቤት

የRaxio የዳታ ማዕከል፣ 6ኛ ፎቅ፣ ኤ4 ህንጻ፣ 379 ኬፕ ቬርዴ መንገድ፣ ቦሌ ክፍለ ከተማ፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

ኤክስፐርቶቻችን/ሙያተኞቻችንን ያናግሩ

ስለ አገልግሎቶቻችን እና የራሲዮ የዳታ ማዕከላት/Raxio Data Centres እንዴት ለንግድ ስራዎ ድጋፍ ሊያደርጉልዎ እንደሚችሉ በተመለከተ የበለጠ ማወቅ ይፈልጋሉ? ለጥያቄዎችዎ በደስተኝነት መልስ ለመስጠት ዝግጁ ነን። ቅጾቹን ይሙሉ እና በተቻለ ፍጥነት እናገኝዎታለን።