Raxio ኢትዮጵያ ስራዎቹን በ2021 ዓ.ም ይጀምራል

Raxio ኢትዮጵያ የTier III ኒውትራል አስተላላፊ የዳታ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ሲሆን በአዲስ አበባ ዳርቻ የሚገኝ ሆኖ የተቋቋመው የአንዳንድ የምስራቅ አፍሪካ ግዙፍ የሶፍትዌር ኩባንያዎች መገኛ የሆነችው ኢትዮጵያን በፍጥነት እያደገ የመጣ የቦታ ለቦታ ግንኙነት ፍላጎት ተቀያያሪ የSME ስነ ምህዳር ፍላጎቶች ለማሟላት ነው።

መገኛ ቦታ

አይሲቲ ፓርክ
በአዲስ አበባ ዳርቻ
ከዋናው የፋይበር መስመር ትይዩ

ግንኙነት

የTier III ደረጃ
በአንድ ራክ ከ2 – 21 kW እስከ 400 ራኮችን
የሚያስተናግድ

ኢንዱስትሪዎች

ድርጅት
የፋይናንስ
ቴሌኮሞች
ሚዲያ
CDNኖች

የቦታ ለቦታ ግንኙነት ፍላጎት በፍጥነት እያደገ የመጣ እና በቴሌኮሙኒከተሸንስ ምህዳር አዳዲስ ገቢዎች እየተፈጠሩ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የመጀመሪያ የዲጂታል ሽግግር ደረጃ ላይ ደርሷል።

የግንኙነት አገልግሎቶች

ስራውን በ2021 ዓ.ም 3ኛ ዕሩብ አመት የሚጀምረው Raxio ኢትዮጵያ ለደንበኞቹ የአይቲ መሳሪያዎቻቸው በከፍተኛ ደረጃ የሚጠቀሙበት ቦታ፤ የኢንዱስትሪውን ተመራጭ ቴክኖሎጂ፣ ደህንነት፣ የAC/DC የሀይል ተስማሚነት እና አለመቆራረጥን በተሟላ ሀሁኔታ የያዘ ተገጣጣሚ አገልግሎት መስጫ ያቀርባል። ደንበኞችን በልዩ ሁኔታ በተዘጋጁ የmeet-me ክፍሎች አማካኝነት ከአገር ውስጥ እና አለም አቀፍ አስተላላፊዎች እና ሌሎች ደንበኞች ጋር ወሰን ተሸጋሪ ግንኙነት እንዲያደርጉ የሚያስችል መሆኑ Raxio ኢትዮጵያን የአገሪቱ አጠቃላይ የዲጂታል ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት እንዲሆን ያስችለዋል።

የቦታ ለቦታ ግንኙነት

ስለ እኛ

ኒውትራል አስተላላፊ የዳታ ማዕከላችን አላማ ተኮር ሆኖ የተገነባ እና የተረጋገጠ የTier III ደረጃዎች ያሉት እንዲሁም 99.99% የአየር ሰዐት እና ተመራጭ ደረጃ ያለው መሳሪያ የሚያቀርብ ማዕከል ነው።

ማዕከሎቻችን ሁሉንም ለተልዕኮ ወሳኝ የአይቲ መሰረተ ልማቶች በቀን ለ24 ሰዐት/በሳምንት ለ7 ቀናት ያለ ምንም መቆራረጥ ለማስተናገድ እንዲቻል ለደንበኞች ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸው፣ እርስ በርሳቸው የተገናኙ ቦታዎችን ያቀርባሉ እንዲሁም እስከ 400 ራኮች የሚያስተናግዱ ቦታዎችን ያቀርባሉ።

ኒውትራል አስተላላፊ

ደንበኞችን ከተለያዩ አስተላላፊዎች ጋር እንዲገናኙ እና ከአስተላላፊዎች መካከል እንዲመርጡ ያስችላቸዋል።

የTier III ደረጃዎች

በቀን ለ24 ሰአት/በሳምንት ለ7 ቀናት ያልተቆራረጠ አገልግሎትን ለማረጋገጥ ያለ ምንም የመቆራረጫ ቦታ ተከታታይና ያልተቆራረጠ አገልግሎት ያቀርባሉ።

ተገጣጣሚ

በአገልግሎት መስጫው ውስጥ ፍላጎቶች በሚጠይቁት መሰረት እያደገ ከሚሄድ አቅም ጋር ወቅታዊና የወደፊት የደንበኞች ፍላጎቶችን ለማሟላት የተዘጋጁ ባለ ፌዝ አቅም ጥቅል መስመሮች።

PUE

1.3 የዲዛይን PUE ረሺዮ

ማቀዝቀዣ

ሀይል ቆጣቢ የአስተላላፊ መያዣ ያለው በተዘዋዋሪ ሙቀት እንዳይጨምር የሚያደርግ የማቀዝቀዣ ቴክኖሎጂ።

የሀይል ስርጭት

በባስባሮች ሀይል በሚያገኙ ተያያዥ ተሰቃይ መስመሮች አማካኝነት የሚደረግ የሀይል ስርጭት

የሀይል ዴንሲቲ

በአንድ ራክ ከ1 kW እስከ 21 kW ራኮችን የማስተናገድ አቅም ያለው

ራኮች

እስከ 58U. ተስማሚ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን የሚያቀርቡ መደበኛ 600 x 1200 ሚሜ ራኮች

ቁጥጥር

ከፍተኛ አፈጻጸምን ለማረጋገጥ እና ብልሽቶችን ፈልጎ ለማግኘት በቀን ለ24 ሰዐት/በሳምንት ለ7 ቀናት የሚደረግ.

ደህንነት

የሳይት ላይ ደህንነትን ለማረጋገጥ በቀን ለ24 ሰዐት/በሳምንት ለ7 ቀናት የሚደረግ የCCTV ቁጥጥር። በመግቢያና ሰርቨሮች መካከል እስከ 7 ዙሮች የሚሰራ አካላዊ ደህንነት።

ታሪካችን

የRaxio የዳታ ማዕከል በአዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ በቅርቡ ስራውን የሚጀምር የድርጅት ደረጃ ያለው የዳታ ማዕከል ነው።

Raxio በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ድርጅት እና የአስተላላፊ ደረጃ ያለው የዳታ ማዕከል አገልግሎት መስጫን ያንቀሳቅሳል። Raxio የተመሰረተው በ2018 ዓ.ም በመላው ምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ የዲጂታል ኢኮኖሚ መሰረት ለመጣል የተቋቋመው የRoha Group ኩባንያ በሆነው በFirst Brick Holdings (“FBH”) ነው። Roha በመላው አፍሪካ አዳዲስ የንግድ ድርጅቶችን የሚገነባና የሚያቋቁም የUS Greenfield የኢንቨስትመንት ኩባንያ ነው።

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የዲጂታል ሽግግር በፍጥነት እያደገ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የዳታ ማዕከሉ የሚገነባው ይህን ሸግግግር የሚደግፍ ዳታ በዳታ ቋት መቀመጥና 100% ያክሉን ጊዜ በትክክል መገኘትና ጥቅም ላይ መዋል በሚችልበት መልኩ ለመጠነ ሰፊና እያደጉ የመጡ የአገልግሎት መስጫዎች ፍላጎቶችን ለማሟላት ነው። የዳታ ማዕከሉ በ2021 ዓ.ም ሲከፈት በኒውትራል አስተላላፊነት የሚሰራና በሙሉ አቅሙ መስራት ሲጀምር እስከ 400 ራኮችን የማስተናገድ አቅም ያለው በኢትዮጵያ በአይነቱ የመጀመሪያ፣ ብቸኛ የTier III ማረጋገጫ ያለው የአገልግሎት መስጫ ሆኖ ያገለግላል።

ተጨማሪ መረጃ ያግኙ

Raxio ለፋይናንስ አገልግሎቶች፣ የመንግስትና ከአነስተኛ እስከ መካከለኛ ድርጅቶች (SMEs) የዳታ ቋት፣ የንግድ ስራ ቀጣይነትና የአደጋ ፍላጎቶቻቸውን በማሟላት አዳዲስ እድሎችን ይከፍትላቸዋል።

ወለላ ሀይለስላሴ

የኢትዮጵያ አገራዊ ዳይሬክተር

ከእነ ማን ጋር አብረን እንደምንሰራ

Raxio ለአገልግሎት መስጫዎቹ የዲዛይንና ግንባታ ስራ ከዩኬ Future-techን፣ እና ከኢትዮጵያ Yema Architecture of Ethiopiaን ተመራጭ ደረጃ ያላቸው የንግድ አጋሮቹ አድርጎ ከመምረጡም በተጨማሪ ስራ ሲጀምርም ከፍተኛ አቅሙን ተጠቅሞ ለመስራትና የስራ እንቅስቃሴውን ለማካሄድ ጠንካራና ልምድ ያለው የአስተዳደር ቡድን አቋቁሟል።

የኢንቨስትመንት አጋሮች

በእውቀት ታፈረ

የራክሲዮ/ Raxio ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስኪያጅ

በዕውቀት የራክሲዮ ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሲሆኑ የተቋሙን ስትራቴጂዎች ተፈጻሚ የማድረግ እና የዕለት ተዕለት ተግባራቱን የማስተዳደር ኃላፊነት አለባቸው።

በዕውቀት በቴሌኮም፣ በመረጃ ቴክኖሎጂ (IT) እና በፊንቴክ(FINTECH) ከ19 ዓመት በላይ የሆነ የአመራር እና የኢንዱስትሪ የስራ ልምድ አላቸው። ስራ  የጀመሩት በኢትዮ ቴሌኮም ሲሆን በተቋሙ  የፕሮዳክት እና  እና ሰርቪስ ሥራ አስኪያጅ በመሆን አገልግለዋል፣ ከዚያ በኋላ በ CIT ኮሙኒኬሽን በሽያጭ ዳይሬክተርነት፣ በኢብር ሞባይል ፋይናንሻል ሰርቪስ (Ebirr MFS) ውስጥ በቺፍ ኦፕሬሽን ኦፊሰርነት (COO) እንዲሁም  በቻናል ቫስ/ ChannelVAS  ውስጥ በካንትሪ ማናጀርነት አገልግለዋል። በዕውቀት በራክሲዮ ያለንን ተልዕኮ ለማገዝ በቴክኖሎጂ፣ በንግድ ስራ ልማት እና በስራ አስተዳደር የካበተ ልምድ ይዘውልን መጥተዋል።

 

በቴሌኮሙኒኬሽን እና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የድህረ ምረቃ ተቋም MBA እንዲሁም ከጅማ ዩኒቨርስቲ በቢዝነስ ማኔጅመንት BA ድግሪ አላቸው።

ኤክስፐርቶቻችን/ሙያተኞቻችንን ያናግሩ

የRaxio የዳታ ማዕከል፣ 6ኛ ፎቅ፣ ኤ4 ህንጻ፣ 379 ኬፕ ቬርዴ መንገድ፣ ቦሌ ክፍለ ከተማ፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

ስለ አገልግሎቶቻችን እና የራሲዮ የዳታ ማዕከላት/Raxio Data Centres እንዴት ለንግድ ስራዎ ድጋፍ ሊያደርጉልዎ እንደሚችሉ በተመለከተ የበለጠ ማወቅ ይፈልጋሉ? ለጥያቄዎችዎ በደስተኝነት መልስ ለመስጠት ዝግጁ ነን። ቅጾቹን ይሙሉ እና በተቻለ ፍጥነት እናገኝዎታለን።