ስለ Raxio በተመለከተ

ሙያዊ ልምዳችን

Raxio Group ተመራጭ የቦታ ለቦታ፣ ወሰን ተሻጋሪ ግንኙነት፣ የፋይበርና አይቲ መሰረተ ልማት አገልግሎቶችን የሚያቀርብ የአፍሪካ መሪ የኬሪየር ኒውትራል የዳታ ማዕከል አንቀሳቃሽ ነው። በአካባቢያዊ የገበያ እውቀታችን እና አለም አቀፍ የኢንዱሰስትሪዎች ሙያተኞቻችን እና አጋሮቻችን እየታገዝን ለአፍሪካ የዲጂታል ኢኮኖሚ በመሰረት ጣይነት የሚያገለግሉ እርስ በርሳቸው በኔትወርክ የተገናኙ የዳታ ማዕከላትን ገንብተን እናንቀሳቅሳለን።

የዳታ ማዕከሎቻችን ለፈጠራ የቴክኒክ መሰረቶችን የሚያቀርቡ አላማ ተኮር መሰረተ ልማት ከመሆናቸውም በተጨማሪ ለአፍሪካ ኢኮኖሚ እድገትና ወደ ዲጂታል ሽግግር ድጋፍ የሚያደርጉ የመሰረተ ልማት ድርጅቶች ናቸው።

ባህላችን

የአፍሪካ ሰፊ የዲጂታል ተጠቃሚ ማህበረሰቦች የሞባይል ስልክ አጠቃቀም እያደገ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የዳታ ፍጆታና ፍላጎትም በአስገራሚ ፍጥነት እያደገ ይገኛል። ይህን ዲጂታል ኢኮኖሚ ለመደገፍ እና በደንበኞች የሚፈለጉ ፍላጎቶችና አገልግሎቶችን ለማቅረብ ለድርጅቶች እጅግ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ አስተማማኝ እና ከፍተኛ አፈጻጸም ያለው የዳታ ቋት/ማዕከልና ማቀነባበሪያ ማቋቋም እንደሚያስፈልጋቸው እናምናለን።

ለአፍሪካ የዲጂታል ሽግግር አቅም መፍጠር

የRaxio Group የዳታ ማዕከላት በአይነታቸው በክፍለ አህጉሪቱ የመጀመሪያ ናቸው። የTier III አገልግሎት መስጫዎቻችን ለተልዕኮ ወሳኝ የሆኑ ሲስተሞች በከፍተኛ ደረጃ አስተማማኝ ለማድረግ 99.99% ያልተቆራረጠ የአየር ሰአት ይሰጣል። ደንበኞች አስተማማኝ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ተከታታይ የ24/7 አገልግሎት ማግኘት መቻላቸውን በማረጋገጥ ከፍተኛ ጥራት ያለው መሳሪያና ሙያዊ ቁጥጥር የሚደረግባቸው አገልግሎት መስጫዎች እናቀርባለን። እንደ ኬሪየር ኒውትራል የዳታ ማዕከላት በተጨማሪም ሁሉንም አይነት መስፈርቶች ለማሟላት ለደንበኞች የተለያዩ አይነት የግንኙነት አማራጮችን እናቀርባለን።

በRaxio Group ባለፉት 3 አመታት ውስጥ መዳረሻዎቻችንን እያስፋፋን ከመሆኑም በተጨማሪ በመላው አህጉሪቱ ውስጥ ከ10-12 አገልግሎት መስጫዎች ለመገንባት በሂደት ላይ ነን። የዳታ ማዕከላቶቻችን የሚቋቋሙት በመላው አፍሪካ የሚደረገውን የኢኮኖሚ እድገት፣ ማህበራዊ ልማትና የዲጂታል ትራንፎርሜሽን ለማስቀጠል ነው።

የአመራር ቡድናችን

ሮበርት ሙሊንስ/Robert Mullins

ማኔጂንግ ዳይሬክተር

ሮበርት የRaxio Group ማኔጂንግ ዳይሬክተር ናቸው። በመላው አፍሪካ የRaxio የዳታ ማዕከላት ስትራቴጂያዊ የእቅድ ዝግጅትን ፣ የማዕከላቱ መስፋፋትን የመምራት ኃላፊነት የተሰጣቸው ከመሆኑም በተጨማሪ ቡድኑ ከአለም አቀፍ እና ክፍለ አህጉራዊ ደንበኞችና አጋሮች ትስስር ጋር የሚያካሂደውን ግንኙነት ያስተዳድራሉ።

ሮበርት/Robert በተጨማሪም በአፍሪካ በመላ አህጉሪቱ በአዳዲስ ኩባንያዎች ላይ ኢንቨስት በማድረግና በመገንባት ትርፋማ የንግድ ድርጅቶችን የሚያቋቁም የዩኤስ ድርጅት የሆነው የRoha Group አጋር ናቸው። Roha ከ2018 ዓ.ም መግቢያ ጀምሮ በRaxio Group ስር የኢንቨስትመንት ልማትe በማቋቋም እየመራ ይገኛል።

Roha እና Raxio ከመቀላቀላቸው አስቀድሞ ሮበርት/ Robert የConfidex፣ የከፍተኛ የቴክኖሎጂ እድገት ኩባንያ የሆነው የSmart Mobility የንግድ ድርጅት ዋና የፋይናንስ ኦፊሰር እና ኃላፊ የነበሩ ከመሆኑም በተጨማሪ የትራንስ አትላንቲክ ሽርክና ድርጅት የሆነው የLogispring አጋር የነበሩ ሲሆን በድርጅቱ የተለያዩ የፖርትፎሊዮ ኩባንያዎች ውስጥ በቦርድ አባልነት አገልግለዋል። ሮበርት/ Robert የባንክ ስራ ኢንቨስት ማድረግ ሙያቸውን የጀመሩት በSchroder Salomon Smith Barney ነበር።

ሮበርት/ Robert ከለንደን የኢኮኖሚክስ ትምህርት ቤት/ London School of Economics በምርምር ስራዎች በማዕረግ በኤምኤስሲ የተመረቁ ከመሆኑም በተጨማሪ ከዳርትማውዝ ኮሌጅ/Dartmouth College በምህንድስና የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል።

ብሩክስ ዋሽግተን/Brooks Washington

ዳይሬክተር

ብሩክስ/Brooks የRoha Group መስራች ሲሆኑ በሁሉም የRoha Group ፖርትፎሊዮ ኩባንያዎች ውስጥ በቦርድ አባልነት ከማገልገላቸውም በተጨማሪ ቀደም ሲል የJuniper Glass Industries ዋና ስራ አስፈጻሚ ኦፊሰር/ CEO/ ሆነው ሰርተዋል።

በ2013 ዓ.ም Rohaን ከመመስረታቸው በፊት ብሩክስ/ Brooks የMcKinsey & Company አማካሪ የነበሩ ከመሆኑም በተጨማሪ የኩባንያውን መስረሪያ ቤት አርማዎች በጋራ አዘጋጅተዋል። Rohaን ለማቋቋም የተነሳሱት በመላው አህጉሪቱ ያሉ የተለያዩ የማይታለፉ እድሎችን እና እነዚህን እድሎች የሚያሟሉ ተቋማት አለመኖርን ለይተው ካወቁ በኋላ ነበር።

ብሩክስ/ Brooks ከሀርቫርድ ኮሌጅ/ Harvard College በማህበራዊ ጥናቶች ዲግሪ አግኝተዋል።

ፍራንስ ቫንሼክ/Frans Van Schaik

የቦርድ አባል

ፍራንስ የአፍሪካን አሴት ፋይናንስ ካምፓኒ ኢንኮርፖሬትድ ሰብሳቢ እና ዋና ስራ አስፈጻሚ ኦፊሰር ሲሆኑ የRaxio Group ቦርድ አባል ሆነው ያገለግላሉ። ፍራንስ በተጨማሪም የRoha ፓርትነር ናቸው።

ቀደም ሲል የTribute Capital መስራች የሆኑት ፍራንስ የLogispring ማኔጂንግ ፓርትነር የነበሩ ሲሆን በተለያዩ የኢንዱስትሪ ቡድኖች ውስጥ (ጊዜያዊ) ዋና ስራ አስፈጻሚ ኦፊሰር ሆነው ከማገልገላቸውም በተጨማሪ በGilde Investment Funds ጀማሪ ፓርትነር ሆነው ሰርተዋል ፣ እንዲሁም ከዚህ በፊትና በመካከል የተለያዩ የንግድ ድርጅቶች (ተባባሪ) መስራች ነበሩ።

ፍራንስ ከአምስተርዳም ዩኒቨርሲቲ በታሪክ ቢ.ኤ. እና ኤል.ኤል.ኤም. ከማግኘታቸውም በተጨማሪ በአለም አቀፍ ግንኙነት ከቪዬና ዩኒቨርሲቲ በድህረ ምርቃ ዲፕሎማ ተመርቀዋል።

 

በርናርድ ጂኦጌጋን/Bernard Geoghegan

የቦርድ አባል

በርናርድ የRaxio Group የቦርድ አባል ሆኖ የሚያገለግል ሲሆን በበርካታ የአማካሪነት ሚናዎች ውስጥ ይሠራል።

በመረጃ ማዕከል ኢንዱስትሪ ውስጥ ከፍተኛ የስራ ኃላፊነቶችን በመያዝ ሲሰራ ቆይቷል ፣ የአውሮፓ የማእከላዊ ምስራቅና የአፍሪካ ዲጂታል ሪያሊቲ ዋና ስራ አስፈፃሚ እና ምክትል ፕሬዚዳንት በመሆን የኩባንያውን የኦፐሬሽን እና የኮርፖሬት ሥራዎችን አስተዳድሯል ፣ በተጨማሪም የColt መረጃ ማዕከል አገልግሎቶች ሥራ አስፈፃሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ፣ ለአየርላንድ ገበያ የጋራ መገኛ እና በዋነኛነት የሚተዳደሩ አገልግሎቶችን የሚያቀርብ የሞዱላር የመረጃ ማዕከል አቅራቢ የሆነው የServecentric Ltd ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ እንዲሁም ፣ የInterxion አየርላንድ እና የInterxion Deutschland GmbH ጊዜያዊ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሆኖ አገልግሏል።

በርናርድ የመረጃ ማዕከል ኢንዱስትሪን ከመቀላቀሉ በፊት ለብዙ የአለም ኮርፖሬሽኖች የተለያዩ የአይ.ቲ.  አያያዝ ፣ ኦፕሬሽኖች እና የሶፍትዌር ማበልጸግ ሚናዎችን አካሂዷል።

ባቪክ ፓትኒ/Bhavik Pattni

የኢንቨስትመንት ሙያተኛ

ባቪክ/Bhavik በRoha Group ውስጥ በፕሮጀክት ስራ አስኪያጅነት እና የኢንቨስትመንት ሙያተኝነት እያገለገሉ ሲሆን አዳዲስ እድሎችን የመገምገም እና የድርጅቱን የፖርትፎሊዮ የንግድ ስራ ድርጅቶች ልማትን የማስተዳደር ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል። ባቪክ/Bhavik የRaxio Group ተባባሪ አደራጅ ከመሆናቸውም በተጨማሪ በRaxio Group ውስጥ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ በልማት ኃላፊነታቸው ላይ በንቃት እየሰሩ ይገኛሉ።

ቀደም ሲል ባቪክ/Bhavik በEast African የግል ኢኩዊቲ ፈንድ Ascent Capital ውስጥ የሰሩ ሲሆን በዑጋንዳ እና ኬንያ ያሉ የኢንቨስትመንት እድሎችን በመለየት የፖርትፎሊዮ ኩባንያዎችን የመሰረቱት በዚህ ድርጅት ውስጥ በሰሩበት ጊዜ ነበር።
ባቪክ/Bhavik ከኖቲንግሀም ዩኒቨርሲቲ/Nottingham University በሜካኒካል ምህንድስና የBEng ዲግሪ አግኝተዋል።

ኬን ሀሪስ/Ken Harris

የፕሮጀክቶች ኃላፊ

ኬን/Ken የRaxio Group የፕሮጀክቶች ኃላፊ ሲሆኑ በመላው አፍሪካ አዳዲስ አገልግሎት መስጫዎችን ለማቋቋም የስምሪት እና የስጋት ጥናት ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል። ኬን/Ken ከአካባቢ ባለስልጣናት እና ባለቤቶች ጋር ግንኙነት በመፍጠር የስትራቴጂያዊ ቦታዎች ግዢን የሚያስተዳድሩ ከመሆኑም በተጨማሪ የእያንዳንዱን አገልግሎት መስጫ አርክቴክቶችና ተቋራጮች ምርጫና የግዢ ሂደት ይመራሉ። ኬን/Ken በእያንዳንዱ ፕሮጀክት የቆይታ ዘመን ውስጥ የRaxioን የፕሮጀክት እቅዶች፣ የጊዜ ሰሌዳዎችና በጀቶች ያስተዳድራሉ።

ኬን/Ken ቀደም ሲል በSchneider Australia ውስጥ የሰሩ ሲሆን በአንዳንድ የአለም መሪ የዳታ ማዕከል ተሳታፊዎች የተለያዩ የኤሌክትሪክ ፕሮጀክቶችን አስተዳድረዋል። ኬን/Ken የስራ ልምዳቸውን ያገኙት ካለፉት የ15 አመታት በላይ የትላልቅ ፕሮጀክቶች የቆይታ ዘመን ልማት፣ በመላው አፍሪካና አውሮፓ ከሞባይል ኢንዱስትሪ አረንጓዴ ልማትና ማስፋፊያ ስራቸው ነው።

ኬን/Ken በቴሌኮሙኒኬሽንስ እና ማርኬቲንግ ዲፕሎማ ያላቸው ከመሆኑም በተጨማሪ የከፍተኛ ፕሮጀክት አስተዳደር የምስክር ወረቀቶችን አግኝተዋል።

ኪሾር ናጉላ/Kishor Nagula

የንግድ ስራ ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት/VP

ኪሾር/Kishor በRaxio Group የንግድ ስራ ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት/VP ሲሆኑ የኩባንያውን እድገት የሚደግፉ የአዳዲስ እድሎችና ገበያዎች ግምገማን ይመራሉ። ኪሾር/Kishor የRaxio Groupን መዳረሻዎች በመላው አፍሪካ በማስፋፋት ላይ ስትራቴጂያዊ ሚና ይጫወታሉ፣ ከደንበኞች ጋር ጠንካራ ግንኙነቶችን መመስረትን ያግዛሉ እንዲሁም Raxio የዳታ ማዕከላት አገልግሎቶች ፍላጎትን ማሟላት መቀጠሉን ያረጋግጣሉ።

ኪሾር/Kishor ቀደም ሲል አዲስ በሚፈጠሩ ገበያዎች ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራው የቡቲክ ማማከር አገልግሎቶች ኩባንያ በሆነው በCaribou Digital በዳይሬክተርነት ያገለገሉ ሲሆን የግሉ ዘርፍ፣ መንግስታትና ፋውንዴሽኖች የዲጂታል ውጤቶችና አገልግሎቶች ትግበራን አግዘዋል። ኪሾር/Kishor ከ30+ በላይ አገሮች የሰሩ ሲሆን በዩኤስ፣ ከሰሀራ በታች አፍሪካ እና በደቡብ እሲያ መጠነ ሰፊ የስራ ልምድ አካብተዋል። ከዚህ በፊት የBooz Allen Hamilton ስትራቴጂያዊ አማካሪ ሆነው ሰርተዋል።

ኪሾር/Kishor ከዲዩክ ዩኒቨርሲቲ/Duke University በMBA፣ ከጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ/ John Hopkins University በMA እና ከዊሊያምና ሜሪ ኮሌጅ/College of William and Mary በBA ተመርቀዋል።

አሊ ማልሂ/Ali Malhi

የፋይናንስ ምክትል ፕሬዝዳንት/VP

አሊ/Ali ከRoha Group የፋይንስ ስራ አስኪያጅነት በሽግግር የመጡ የRaxio Group የፋይናንስ ምክትል ፕሬዝዳንት ናቸcው። አሊ/Ali የኮርፖሬት ፋይናንስን፣ የኢንቬስተር ግንኙነቶችና ሌሎችንም ጨምሮ የRaxio Groupን የዕለት ከእለት የፋይናንስ ግብይት ስራዎችነን ይቆጣጠራሉ።

አሊ/Ali በRoha Group ውስጥ ቀደም ሲል በነበራቸው የስራ ድርሻ የቡድኑን፣ ተቀጽላዎቹን እና የድርጅቱን የኢንቨስትመንት ፈንድ ፋይናንሶች አስተዳድረዋል። በተመሳሳይ ቀደም ሲል የImperial Logisticsን የፋይናንስ ስራ ያስተዳደሩ እንደመሆኑ በFMCG እና F&B ዘርፎች ስር በተለያዩ ብሄራዊ ኩባንያዎች የፋይናንስ ስራ ከ13 አመታት በላይ የስራ ልምድ አግኝተዋል።

አሊ/Ali ከግሪፍዝ ዩኒቨርሲቲ/Griffith University በMBA የተመረቁ ከመሆኑም በተጨማሪ ከሲፒኤ አውስትራሊያ/CPA እውቅና አግኝተዋል።

ጄምስ ባይሩሀንጋ/James Byaruhanga

ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ ዑጋንዳ

ጄምስ/James በአይቲ ኢዱስትሪ ውስጥ ከ20 አመታት በላይ የስራ ልምድ ያላቸው ሲሆን በተለያዩ መሪ የቴሌኮም ኩባንያዎች እና የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢዎች ውስጥ በስራ አስኪያጅነት ሰርተዋል። ጄምስ/James የRaxio ዑጋንዳን የእለት ከዕለት የስራና የንግድ ስራ እንቅስቃሴዎችን ከመቆጣጠር በተጨማሪ ከፍተኛ የጥራት ደረጃ ያለው አገልግሎት መቅረቡን ለማረጋገጥ ከደንበኞች ጋር በቅርበት ይሰራሉ።

ጄምስ/James ስለ ዑጋንዳ የገበያ ሁኔታዎች እና መጠነ ሰፊ የድርጅት ኔትወርክና የቴልኮ ግንኙነቶች ላይ የካበተ ሙያዊ ልምድ እና እውቀት አላቸው።

ጄምስ/James ቀደም ሲል በአማራጭ የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢነት በመሪነት ጥግ ላይ በሚገኘው በRoke Telkom ውስጥ ዋና አስተዳዳሪነትን፣ ዋና የአሰራር ኦፊሰርነት እና ዋና የቴክኖሎጂ ኦፊሰርነትን ጨምሮ በተለያዩ የስራ መደቦች ላይ አገልግለዋል። ጄምስ/James በዑጋንዳም ሆነ ኬንያ፣ ሩዋንዳ፣ ዛምቢያ እና ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክን በመሳሰሉ አጎራባች አገራት ለRoke የስራ እንቅስቃሴዎች የኩባንያው የቴክኒክ መሰረተ ልማትና የእቅድ ዝግጅት ኃላፊነት ተሰጥቷቸው ነበር።

ጄምስ/James ከRoke የስራ ድርሻ ቀደም ብሎ በMTN Uganda በተለያዩ የቴክኒክ ማማከር የስራ ድርሻዎች ለ5 አመታት እና በዑጋንዳና ጋና Africa Online ውስጥ ለ3 አመታት አገልግለዋል።

ማይንዛ ሙኖ/Mainza Moono

የንግድ ስራ ተንታኝ

ማይንዛ /Mainza የRaxio Group ክፍለ አህጉራዊ የንግድ ስራ ተንታኝ ሲሆኑ በመላው አፍሪካ አህጉር የአዳዲስ ገበያዎች የቅድመ ኢንቨስትመንት የጥንቃቄ ጥረቶች መምራትን የመርዳት ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል። ማይንዛ /Mainza በመላው አፍሪካ የአዳዲስ ፕሮጀክቶች አዋጭነት፣ የንግድ ትርፋማነትና የቁጥጥር ሁኔታ ግምገማን ያግዛሉ።

ማይንዛ /Mainza ወደ Raxio Group ከመቀላቀላቸው በፊት በአፍሪካ በAI የሚመሩ ተጽእኖ ፈጣሪ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን መገንባት ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራው የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ማቋቋሚያ ቅድመ ደረጃ ተባባሪ መስራች ነበሩ። ማይንዛ /Mainza በተጨማሪም ቀደም ሲል በሳንፍራንሲስኮ፣ ጆሀንስበርግ እና ሞሪሺየስ በንብረት አስተዳደርናa የግል ኢኩዊቲ የተለያዩ የኢንቨስትመንት የስራ ድርሻዎች ላይ ሰርተዋል።

ማይንዛ /Mainza ከኦሀዮ ዌስሊን ዩኒቨርሲቲ/ Ohio Wesleyan University በኢኮኖሚክስ ዲግሪ አግኝተዋል።

ኤክስፐርቶቻችን/ሙያተኞቻችንን ያናግሩ

ስለ አገልግሎቶቻችን እና የራሲዮ የዳታ ማዕከላት/Raxio Data Centres እንዴት ለንግድ ስራዎ ድጋፍ ሊያደርጉልዎ እንደሚችሉ በተመለከተ የበለጠ ማወቅ ይፈልጋሉ? ለጥያቄዎችዎ በደስተኝነት መልስ ለመስጠት ዝግጁ ነን። ቅጾቹን ይሙሉ እና በተቻለ ፍጥነት እናገኝዎታለን።