የድረገጽ ፖሊሲዎቻችን

ድንጋጌዎችና የግላዊነት ፖሊሲያችን

የግላዊነት ፖሊሲና የአጠቃቀም ድንጋጌዎች

ሁሉም ሶስቱ የህግ ሰነዶች በልዩ ሁኔታ ለእርስዎ የንግድ ስራ ወይም አሰራር የተጻፉ መሆን አለባቸው። ሰነዶቹን ከሌላ ድረገጽ ላይ ለመገልበጥ የሚደረግ ሙከራ የቅጂ መብትን የሚጥስ በመሆኑ የግላዊነት ህግን ወይም ACLን በመጣስዎ ከባድ ችግር ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ።

ለትላልቅ ወይም ውስብስብ ተቋማት ከአንድ በላይ ፖሊሲ ያስፈልግዎ ስለመሆኑ (ለተለያዩ የስራዎ ወይም የንግድ ስራዎ ክፍሎች፣ ወይም ለተለያዩ ተግባሮች ወይም የስራ እንቅስቃሴዎች) ያጢኑ።

1. የአጠቃቀም ድንጋጌዎች

የንግድ ስራዎ ድረገጽ ያለው ከሆነ ለተጠቃሚዎችዎ እንዴት መንቀሳቀስ እንደሚችሉና እንደማይችሉ ለማሳወቅ የሚያስችሉ የአጠቃቀም ድንጋጌዎች ሊኖሩዎ ይገባል። ይህ የህግ ሰነድ ለIP ጥበቃ ከማድረግ በተጨማሪ ተጠያቂነትዎን ይገድበዋል። ሰነዱ በተጨማሪም ተፎካካዎችን አለማስገባትን ጨምሮ የሚፈቀድና የማይፈቀድ ምግባር/ድርጊትን ይወስናል።

የአጠቃቀም ድንጋጌዎችዎ ወደ ድረገጽዎ በሚገባ በሁሉም ሰው ላይ ተፈጻሚነት ይኖራቸዋል።

2. ድንጋጌዎችና ሁኔታዎች

የድንጋጌዎችና ሁኔታዎች አምስት ባህሪያት አሉ:

  • ለግልጽነትና እርግጠኝነት የምርት ውጤቶች ወይም አገልግሎቶች፣ እና እነዚህ እንዴት እንደሚቀርቡ የተመለከተ ዝርዝር፣
  • ወለድ ማስከፈል እና ክፍያ ለማስፈጸም እዳ ሰብሳቢ ወይም ጠበቃ የመቅጠር መብትን ጨምሮ የክፍያ ድንጋጌዎች፣
  • አስገዳጅ የሸማች ዋስትናዎች እና ተመላሽ የማድረግ ፖሊሲዎ፣
  • አለመግባባትን ለመፍታት እና ወደ ፍርድ ቤት የመሄድ ወጪና እርግጠኝነት ማጣትን ለማስቀረት የሚረዳዎ የአለመግባባት አፈታት፣ እና
  • ጥቅሞችዎን ማስከበሪያ ከኃላፊነት ነጻ መሆንና ተጠያቂነትዎን መገደብ።

ከዚህ በተጨማሪም ድንጋጌዎችና ሁኔታዎች በአውስትራሊያ የሸማች ሕግ/Australian Consumer Law (ACL) የተሰጡዎትን የንግድ ስራ መብቶችዎን ያብራራሉ። ሶስት ዋና ዋና የኦንላይን የንግድ ስራ አይነቶች ያሉ ሲሆን እያንዳንዳቸው የተለያዩ ድንጋጌዎችናa ሁኔታዎችን ይጠይቃሉ።

የአገልግሎት ንግድ ስራ: የደንበኛ ስምምነት
የንግድ ስራዎ አገልግሎቶችን የሚሸጥ ከሆነ የደንበኛ ስምምነት ያስፈልግዎታል። የደንበኛ ስምምነትዎ የሚከተሉትን ይገልጻል፡

  • የሚያቀርቧቸውን አገልግሎቶች;
  •  አገልግሎቶቹን እንዴት እንደሚያቀርቡ; እና
  • የእርስዎን እና የደንበኛዎን ግዴታዎች

ማከፋፈል ወይም የኢ-ንግድ: የሽያጭ ድንጋጌዎችና ሁኔታዎች
እነዚህ ድንጋጌዎችና ሁኔታዎች ሸማቾች ምርቶችዎን በሚገዙበት እርስዎ ማቅረብ ያለብዎትን እና ሸማቾች መጠየቅ ያለባቸውን መረጃዎች ይገልጻሉ። እነዚህ የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ፡

  • አቅርቦት፣
  • የተመላሽ ምንዛሪ ፖሊሲ፣
  • ተጠያቂነትን መገደብ፣ እና
  • የACL መከበር

በአግባቡ የተረቀቁ የሽያጭ ድንጋጌዎችና ሁኔታዎች ክፍያዎችን በማይከፍሉ ወይም ግጭቶችን በሚያስነሱ ደንበኞች ላይ ልዩነት መፍጠር ያስችላሉ።

የገበያ ቦታ: የገበያ ቦታ ድንጋጌዎችና ሁኔታዎች
የገበያ ቦታዎች በተለመዱ ድንጋጌዎችና ሁኔታዎች ስር ለሚነሱ ጉዳዮች እና የሚከተሉትን ጨምሮ ለተጨማሪ ጉዳዮች መፍትሄ የሚሰጡ አጠቃላይ ድንጋጌዎችና ሁኔታዎች ያስፈልጓቸዋል፡
● የተጠቃሚዎች ለድረገጹ ትክክለኛ መረጃ ማቅረብ፤
● የተጠቃሚ ይዘት፣
● IP፣
● በተዋዋይ ወገኖች መካከል የሚደረጉ ህጋዊ ግንኙነቶች፣
● የእርስዎ ግዴታዎች; እና
● የተጠቃሚዎች ግዴታዎቻቸውን ማክበር

3. የግላዊነት ፖሊሲ

ድረገጽዎ የግል መረጃ የሚሰበስብ ወይም የሚጠቀም ከሆነ የግላዊነት ፖሊሲ ያስፈልግዎታል። የግላዊነት ፖሊሲ APPዎችን ለማሟላት ዋነኛው መሳሪያ ነው። የግላዊነት ፖሊሲ የህጉን መከበረር ያረጋግጣል እንዲሁም የግል መረጃን በግልጽና ግልጸኝነት ባለው አኳኋን ያስተዳድራል። የግላዊነት ፖሊሲው በፖሊሲው ስር የሚሸፈኑ ርዕሰ ጉዳዮችን መወሰን እና የAPPዎች መከበርን ለማረጋገጥ የAPP ተቋም መተግበር ያለበትን አሰራሮች፣ ሥነ ሥርአቶችና ሲስተሞች/ስርአቶች መግለጽ አለበት።

የግላዊነት ፖሊሲዎ የሚከተሉትን ማካተት አለበት:

  • እርስዎ የሚሰበስቡትን የግል መረጃ;
  • መረጃውን እንዴት እንደሚጠቀሙበትና እንደሚገልጹ; እና
  • መረጃውን እንዴት እንደሚያስቀምጡ።

ፖሊሲው የደንበኛው የሚከተሉትን መብቶች ይገልጻል:

  • ከእርስዎ ጋር ግንኙነት የማድረግ;
  • አባልነቱን የመሰረዝ; እና
  • ቅሬታ የማቅረብ .

የግላዊነት ፖሊሲውን በመጣስ ምክንያት የሚጣሉ በመጠን የተወሰsኑ ቅጣቶች ያሉ በመሆኑ ፖሊሲው መከበር አለበት። ለተጠቃሚዎች የማስታወቂያ መሳሪያዎችን ለመላክ ካቀዱ የትኛውንም የማጭበርበር ህግን መጣስን ለመከላከል እና ከፍተኛ ደረጃ የደንበኛ አገልግሎት መቅረብን ለማረጋገጥ እነዚህ በደdንበኞች መልእክት ዝርዝርዎችዎ ስር እንደሚካተቱ ለደንበኞችዎ ማሳወቅ ጥሩ ነው።

የድረገጽ ህጋዊ ሰነዶችን በተመለከተ በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች
ጥያቄ: የድረገጽ ከኃላፊነት ነጻ መሆን ምንድን ነው?
መልስ: የድረገጽ ከኃላፊነት ነጻ መሆን ከህግ ተጠያቂነት ጋር ብቻ ተያያዥነት ያላቸው የተለያዩ ጠቅላላ የድረገጽ ድንጋጌዎችና ሁኔታዎች ናቸው። ከዚህ በተጨማሪም ችግሮች በሚፈጠሩበት ወቅት የእርስዎን የተጠያቂነት ገደቦች የሚገልጽ ከኃላፊነት ነጻ መሆኛ መጻፍ አለብዎ።

ጥያቄ: ተቀባይነት ያለው አጠቃቀም ፖሊሲ ምንድን ነው?
መልስ: ይህ ፖሊሲ የተለያዩ በንግድ ድርጅቱ ተፈጻሚ የሚደረጉ ተጠቃሚዎች ኔትወርክ፣ ድረገጽ ወይም ሲስተም የሚጠቀሙባቸውን ዘዴዎች የሚገድቡ ህጎችን ይይዛል። ፖሊሲው በጠቅላላው የመረጃ ዋስትና ፖሊሲዎችን ይይዛል።

LegalVision እንዴት ሊረዳኝ ይችላል?
LegalVision ለንግድ ድርጅቶችና ግለሰቦች ለድረገጾች የግላዊነት ፖሊሲዎችን፣ የአጠቃቀም ድንጋጌዎችን፣ እና ድንጋጌዎችና ሁኔታዎችን ጨምሮ የኦንላይን የህግ ሰነዶችን ማርቀቅን ጨምሮ ተያያዥነት ያለው የኦንላይን የህግ ምክር ያቀርባል። ድረገጽዎ የህግ መስፈርቶችን ማሟላቱን የሚያረጋግጡ ልምድ ያላቸው የንግድ ስራ የህግ ሙያተኞች አሉን። ለLegalVision በስልክ ቁጥር 1300 544 755 ይደውሉ።

ኤክስፐርቶቻችን/ሙያተኞቻችንን ያናግሩ

ስለ አገልግሎቶቻችን እና የራሲዮ የዳታ ማዕከላት/Raxio Data Centres እንዴት ለንግድ ስራዎ ድጋፍ ሊያደርጉልዎ እንደሚችሉ በተመለከተ የበለጠ ማወቅ ይፈልጋሉ? ለጥያቄዎችዎ በደስተኝነት መልስ ለመስጠት ዝግጁ ነን። ቅጾቹን ይሙሉ እና በተቻለ ፍጥነት እናገኝዎታለን።

ቆይ በናተህ...
ሁሉም ተጠናቀቀ!
ውይ! የሆነ ስህተት ተከስቷል. እባክዎ ዳግም ይሞክሩ.