9 March 2021

የራክሲዮ የዳታ ማዕከል ግንባታ በይፋ ተጀመረ

አዲስ አበባየካቲት 30/2013 በአፍሪካ አንጋፋው ፓን አፍሪካዊ የዳታ ማዕከል ገንቢና ኦፐሬተር ተቋም የራክሲዮ ግሩፕ በአዲስ አበባ አይ.ሲ.ቲ ፓርክ ውስጥ የሚሰራውን የዳታ ማዕከል የመሰረት ድንጋይ አስቀመጠ።

ሲጠናቀቅ በልህቀቱና አስተማማኝነቱ በሀገራችን ቀዳሚው certified Tier-3 colocation የሚሆነውን ዳታ ማእከል ግንባታ ማስጀመሪያ መሰረተ ድንጋይ ማስቀመጡም የሚዲያ ባለሞያዎችን ጨምሮ የኢንዱስትሪ ልማት ኮርፖሬሽን ፣ የማ አርኪቴክቸር እና የራክሲዮ ግሩፕ ተወካዮች እንዲሁም የተለያዩ ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በአይ.ሲ.ቲ. ፓርክ ተካሂዷል።

በዝግጅቱ ላይ በዘርፉ የሚሰሩ ባለሙያዎች እና የተቋማት ተወካዮች የዳታ ማዕከሉን ፋይዳ እና አስተዋጽዖ አስመልክተው አስተያየቶቻቸውን ያካፈሉ ሲሆን የራክሲዮ ግሩፕ ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙሊንስ በበኩላቸው የፕሮጀክቱ ሚና ኢትዮጵያ ለምትገነባው የዲጂታል ኢኮኖሚ እና ለምትዘረጋው ዲጂታል መሠረተ ልማት ትልቅ ግብዓት እንደሚሆን ተናግረዋል።

ፕሬዚዳንቱ አክለውም “ከጠለቀ የዲዛይን ሂደት በኋላ በኢትዮጵያ ከሚኖሩን ተመሳሳይ ፕሮጀክቶች የመጀመሪያ የሆነውን ይህንን ማእከል ግንባታ ስንጀምር በደስታ ነው። ይህም ሂደት በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር የሚገኙ ደንበኞችን እና እያደገ ያለውን ዘመናዊ የዲጂታል መሰረተ ልማት አገልግሎት ፍላጎትን ያገናዘበ ነው። የዳታ ማዕከሉ በኢንዱስትሪው አዲስ ምዕራፍ መክፈቻ ተደርጎ የሚወሰድ ሲሆን የአይ.ሲ.ቲ. ዘርፍ እድገትን ከማገዝ በተጨማሪ ክህሎት የሚጠይቁ የስራ እድሎችን በመፍጠርም በኩል አስተዋፅኦው ከፍ ያለ ይሆናል” ብለዋል።

Robert Mullins

ሮበርት ሙሊንስ የራክሲዮ ግሩፕ ፕሬዚዳንት

ለዚህ ዳታ ማዕከል ግንባታ ራክሲዮ አብረውት የሚሰሩ ልምድ ያላቸው የዲዛይን የኢንጂነሪንግ እና የኮንስተራክሽን ባለሙያዎች የሆኑትን የዩናይትድ ኪንግደሙ ፊውቸር ቴክ እና የኢትዮጵያው የማ አርክቴክቸርን ቀጥሯል።

በኢትዮጵያ የዳታ ማዕከል የሚጠቀሙ እና እድገታቸው በአይ.ቲ መሰረተ ልማት ላይ የተመረኮዙ ተቋማት በአብዛኛው በከፍተኛ ወጪ ምቹ ወዳልሆኑ የመፍትሔ አማራጮች መሄዳቸው በኢትዮጵያ ለዚሁ ፍላጎት ብቻ ተብሎ የተሰራ በብቁ ባለሙያዎች የሚተዳደር የዳታ ማዕከል ማስፈለጉ ማሳያ ነው።

በ2014 አጋማሽ ግንባታው ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቀው ማዕከል በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ እጅግ የዘመነ እና የተሟላ አገልግሎትን ማቅረብ የሚችል ሲሆን በውስጡ እጅግ ምቹ ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ ሆኖ ዘመናዊ የሆነ ቴክኖሎጂ እና ዘመኑ ያፈራቸውን አዳዲስ መሳሪያዎችን እንዲሁም ተደራራቢ የሆነ የኤ.ሲ./ዲ.ሲ. የኃይል አማራጮችን በመያዝ ለደንበኞቹ በተሟላ መልኩ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አገልግሎት ይሰጣል። ይህ ማዕከል በተለየ ሁኔታ የተዘጋጁ ክፍሎች በመጠቀም የአገር ውስጥና የዓለም አቀፍ የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢዎችን እና ደንበኞችን የሚያገናኝ ሲሆን ይሄም ራክሲዮ ኢትዮጵያን የአገሪቱ ዲጂታል ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት አካል እንዲሆን ያስችለዋል።

የዳታ ማዕከሉ ከአዲስ አበባ እምብርት በቅርብ ርቀት ላይ አለም አቀፍ ስታንዳርድን እና የራክሲዮን ከባቢያዊ ሁኔታ እና ተፈጥሮ ላይ ያለን ጫና ማሳነስ መርህ በተከተለ መንገድ የሚገነባ ነው። በኢትዮጵያ በፍጥነት እያደገ ካለው የኢንተርኔት አጠቃቀም እና በሪፎርም ሂደት ላይ ካለው የቴሌኮሙኒኬሽን ዘርፍ ጎን ለጎን የራክሲዮ ዳታ ማዕከል ማናቸውንም የአይ.ቲ. ሲስተማቸውን በምቹ እና በተጠበቀ መንገድ ማስተዳደር የሚፈልጉ ደንበኞችን ፍላጎት ማሟላት ይችላል።

የራክሲዮ ኢትዮጵያ ዳታ ማዕከል አሉ በተባሉ የግንባታ ዘዴዎች እና በፕሪ-ፋብ ግብአቶች የሚገነባ ሲሆን ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ የደንበኞቹን የሀይል ፍላጎት ለማሟላት አቅርቦቱን እስከ 3.0MW (~700 ራክስ) የማድረግ እቅድ አለው።

ራክሲዮ ኢትዮጵያ በታህሳስ ወር 2012 ዓም ከኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሞ በይፋ እንቅስቃሴ ጀምሯል። ይህንን ተከትሎም የኢንቨስትመንት ዕቅዱን ተግባራዊ የሚያደርግበት የመስሪያ ቦታ በአይ.ሲ.ቲ ፓርክ ተረክቦ የግንባታ ስራውን በማካሄድ ላይ ይገኛል።

 


 

ስለ ራክሲዮ ግሩፕ

ራክሲዮ የአሜሪካ ኩባንያ የሆነው ሮሃ ግሩፕ ኢንቨስትመንት ኩባንያ አካል እና በተለያዩ የአፍሪካ አገራት በሚገኙ የንግድ ድርጅቶች ላይ በኃላፊነት ስሜት መዋዕለ ንዋይ የሚያፈስ ኩባንያ ነው። ግሩፑ በምስራቅና ደቡብ አፍሪካ ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ፣ ራስ ገዝና ቲር-3 የሆኑ የዳታ ማዕከል ስራዎችን በራክሲዮ ብራንድ አማካኝነት ያከናውናል። የመጀመሪያው ኢንቨስትመንት የሆነው የዩጋንዳ ዳታ ማዕከል በአሁኑ ወቅት ግንባታው ወደ መገባደዱ ሲሆን በቀጣዮቹ ሁለት ወራት ውስጥ ወደ ስራ እንደሚገባ ይጠበቃል።

ራክሲዮ ዳታ ሴንተር ኃ.የተ.የግ.ማ. በኢትዮጵያ በታህሳስ 2012 ዓ.ም. የተቋቋመ ሲሆን በ2014 አጋማሽ ግንባታ ጨርሶ ስራ እንደሚጀምር ይጠበቃል። በተጨማሪም ከሰሞኑ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በይፋ ያስጀመረው ተመሳሳይ ፕሮጀክት ግሩፑ በፍጥነት ኢንቨስትመንቱን እያስፋፋ ስለመቀጠሉ ማሳያ ሆኖ ሊጠቀስ ይችላል። በ2015 ዓ.ም. በመላው ምስራቅ አፍሪካ እና ደቡብ አፍሪካ የሚያካልል የዳታ ማዕከላት መረብ ለመዘርጋት የሚያስችለውን የኢንቨስትመንት እቅዶች አዘጋጅቷል።

ለተጨማሪ መረጃ www.raxiogroup.com ይጎብኙ።

 

ኤክስፐርቶቻችን/ሙያተኞቻችንን ያናግሩ

ስለ አገልግሎቶቻችን እና የራሲዮ የዳታ ማዕከላት/Raxio Data Centres እንዴት ለንግድ ስራዎ ድጋፍ ሊያደርጉልዎ እንደሚችሉ በተመለከተ የበለጠ ማወቅ ይፈልጋሉ? ለጥያቄዎችዎ በደስተኝነት መልስ ለመስጠት ዝግጁ ነን። ቅጾቹን ይሙሉ እና በተቻለ ፍጥነት እናገኝዎታለን።

ቆይ በናተህ...
ሁሉም ተጠናቀቀ!
ውይ! የሆነ ስህተት ተከስቷል. እባክዎ ዳግም ይሞክሩ.