Raxio Ethiopia launch

21 November 2023 / ዜናዎች

ራክሲዮ የአፍሪካን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና ዲጂታል ኢኮኖሚን የመደገፍ እንቅስቃሴውን በኢትዮጵያ አዲስ የዳታ ማዕከል በማቋቋም ቀጥሏል።

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ ዳር 11/2016 ዓ.ም _ ራክሲዮ የዳታ ማዕከል፤ በመላው አፍሪካ የዘመናዊ ገለልተኛ ዳታ ማዕከሎች አገልግሎት በማቅረብ ግንባር ቀደም የሆነው አዲሱን ተቋሙን በአዲስ አበባ፤ ኢትዮጲያ በይፋ ስራ ማስጀመሩን በኩራት አስታውቋል። በዚህ ወሳኝ ምዕራፍ ራክሲዮ ደህንነታቸው የተጠበቀ፣ ምትክ ያላቸው እና ፈጠራን መሰረት ያደረጉ የዳታ ማዕከል መፍትሄዎችን በማቅረብ እያደገ የመጣውን የቀጠናውን ፍላጎት ለማሟላት ያለውን ቁርጠኝነት ያመለክታል።

በኢትዮጵያ ዋና ከተማ እና የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ማዕከል በሆነችው አዲስ አበባ የሚገኘው አዲሱ የራክሲዮ ደረጃ III እውቅና የተሰጠው ዘመናዊ ዳታ ማዕከል ከምንግዜም በላይ እያደገ ለመጣው የመንግስት እና የግል ተቋማት የዳታ ማዕከል አገልግሎት ፍላጎት ጥያቄዎች አስተማማኝ እና የማይቆራረጥ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ  መፍትሄ በማቅረብ መልስ የሚሰጥ ይሆናል። ማዕከሉ 800 ራኮች እና እስከ 3MW የአይቲ ሃይል ደህንነቱ በተጠበቀ የመሰብሰቢያ ቦታ (Co-Location) አገልግሎት ለመስጠት፣ ሙሉ በሙሉ ምትክ ያለው 24/7 ያለማቋረጥ የሚሰራ የአይቲ (IT) መሰረተ ልማቶች ማኖሪያ ዝግጁ አድርጓል። 

በኢትዮጵያ የራክሲዮ ዳታ ማዕከል ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ በዕውቀት ታፈረ እንደገለጹት ‘’ይህ አገልግሎት በአዲስ አበባ መጀመሩ ለራክሲዮ እና ለሀገራችን ትልቅ ምዕራፍ ነው። ይህ አገልግሎት በኢትዮጵያ የምጣኔ ሀብት ዕድገት ውስጥ ከፍተኛ ሚና የሚጫወት ሲሆን በተለያዩ አካባቢዎች የሚከናወኑ ንግድ ሥራዎችን እና የመንግስት ኤጀንሲዎች የሥራ እንቅስቃሴ የሚያፋጥን እንዲሁም አህጉራዊ እና አለም አቀፍ አገልግሎት እና የይዘት አቅራቢዎችን ወደ ኢትዮጵያ ለመሳብ አጋዥ እንደሚሆን እናምናለን። የማዕከላችን ደረጃ III አለም አቀፍ የምስክር ወረቀት እኛ እየሰጠን ስላለው የአገልግሎት ጥራት መጠን ማሳያ ሲሆን ለደንበኞቻችን ደግሞ ለማናቸውም ንብረቶቻቸው ከፍተኛ ደህንነት አስተማማኝ ማረጋገጫ የሚሰጥ ነው።‘’

የዲጂታል ዕድገት

የራክሲዮ አዲሱ የዳታ ማዕከል ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ለውጥ ያመጣል ተብሎ ይጠበቃል። ገሪቷ በዲጂታል አካታች ሂደት ላይ ትኩረት ሰጥታ የምንትቀሳቀስ በመሆኑ የራክሲዮ ደረጃ III ተቋም አገልግሎት ለአይሲቲ (ICT) መሰረተ ልማት እና በየነ መረብ ከፍተኛ እና አስፈላጊ አስተዋጽኦ ከማበርከት በተጨማሪ የቴክኖሎጂ ጥቅማ ጥቅሞች በመላ አገሪቱ ተደራሽ መሆናቸውን በማረጋገጥ የትምህርት፣ ማህበራዊ እና የንግድ ግብዓቶችን ተደራሽነት ለማሻሻል ይረዳል።  በተጨማሪም የዚህ ተቋም ሥራ መጀመር በአገር ውስጥ ሚንቀሳቀሱ ኢንተርፕራይዞች ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክት እንደሚሆን ይጠበቃል፣ ይህም ወሳኝ የሆኑ የአይቲ መሠረተ ልማቶቻቸውን አስተማማኝ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ሁልጊዜም ምቹ የሆነ የዳታ ማዕከል አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላቸዋል።

እንደ የአገልግሎት አቅራቢገለልተኛ የዳታ ተቋም፣ ራክሲዮ ኢትዮጵያ የሀገሪቷ አንድ የግኑኝነት ማዕክል ሆኖ በማገልገል የተለያዩ ሃገራዊ እና አለም አቀፍ አካላት እርስ በእርስ በማስተሳሰር በቅርበት መረጃ የሚለዋወጡበት የኢኮ ስርዓት (Eco System) ያቀርባል። ድርጅቶች በጣም በተገናኘ ፣ሁልጊዜ በሚሰራ ፣በተለያዩ የፋይበር መስመሮች በተደገፈ፤ የኢንተርኔት አቅራቢዎች አማራጮች በመምረጥ እና እራሳቸውን ከግንኙነት መቆራረጥ በመጠበቅ ተጠቃሚ ይሆናሉ ። በተጨማሪም አንዱ ከሌላው ጋር ለማስተሳሰር የሚረዳው ይህ ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶ የዳታ ፍሰትን ሙሉ በሙሉ በአገር ውስጥ በማድረግ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ድርጅቶች ለኢንተርኔት አገልግሎት የሚያወጡትን ወጪ ለመቀነስ የሚረዳ ነው፤ ድርጅቶቹም ይህንን ቅናሽ ወደ ደንበኞቻቸው በማስተላለፍ የላቀ አገልግሎት እንዲያቀርቡ ያስችላል።

ራክሲዮ ዳታ ማዕከል በኢትዮጰያ ውስጥ ይፋ ስራ መጀመር ከፈጠራ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 የልማት ግብ እና ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ዋና ዋና አላማዎች ጋር ሙሉ በሙሉ የሚጣጣም ነው። በተለይም ፡– 

  • አይሲቲ መሰረተ ልማት፡- ለዲጂታል አካታችነት የአይሲ መሰረተ ልማመረብ በመላ ገሪቷ ማዳረስ እና መሸፈን
  • ሥራ ፈጠራ፡- በአይሲቲ ምርምር እና ሥራ ፈጠራ አማካኝነት የሥራ ዕድል ማሳደግ
  • ዳታ ደህንነት፡- የኢንፎርሜሽን ሴኩሪቲ ሲስተም ደህንነቱ የተጠበቀ፣ አስተማማኝ፣ ጠንካራ እና ለሳይበር ደህንነት ስጋቶች ምላሽ መስጠት የሚችል እንዲሆን ማሻሻል

የራክሲዮ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ሮበርት ሙሊን እንደገለፁት “አዲስ ማዕከል ማስጀመር ረዥም እና አንዳንዴ ከባድ ጉዞ ነውጉዞዉ የትጋት ጠንክሮ የመስራት እና ያለንን አጠቃላይ የራክሲዮ የጋራ እውቀት ያፈሰስንበት ነበር። ይህንን በዓይነቱ ልዩ እና የመጀመሪያ የሆነ ወሳኝ መሠረተ ልማት በኢትዮጵያ ተግባራዊ በማድረጋችን እጅግ ኩራት የሚሰማን ሲሆን የኢትዮጵያን ቀጣይ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና የዲጂታል አካታችነት ጅምር ግቦችን የሚደግፍ እንደሆነ ሙሉ እምነታችን ነው።

ራክሲዮ ኩባንያ በሚቀጥሉት ጥቂት ወራት ውስጥ ለመክፈት ካቀዳቸው በርካታ የዳታ ማዕከሎች ውስጥ ራክሲዮ ኢትዮጲያ የመጀመሪያው ነው። ሮበርት ሙሊንስ አክለው እንደተናገሩት፣ “ይህ ጊዜ ለእኛ እንደ ኩባንያ እጅግ በጣም ደስተኛ የሆንበት ነው። ከሁለት አመት በፊት በኡጋንዳ እንደዚሁ ተመሳሳይ ማዕከላችንን ከጀመርን በኋላ ራክሲዮ ኢትዮጵያ ከአሁን ጀምሮ እስከ 2024 የመጀመሪያ አጋማሽ ድረስ ከምንከፍታቸው ተቋማት ዉስጥ የመጀመሪያው ሲሆን ተቋሞቻችንን በሞዛምቢክ፣ በአይቮሪ ኮስት እና በዲሞክራቲክ ኮንጎ በመቀጠል የምንከፍት ይሆናል። እ.ኤ.አ. በ2024 እና በ2025 መጀመሪያ ላይ እነዚህን እና ተጨማሪ ማዕከሎችን በማስከተል፣ አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የዳታ ማዕከል መሠረተ ልማትን በአፍሪካ ውስጥ ባልተሟላባቸው ገበያዎች ለማቅረብ የገባነውን ቃል ተግባራዊ ማድረጋችንን እንቀጥላለን።‘’

በዘላቂነት መገንባት 

የማዕከላችን ሃይል ቆጣቢ ንድፍ እና የአካባቢ ጥበቃ መርሆቻችን ራክሲዮ ዘላቂ መፍትሄዎች ላይ ያለውን ቁርጠኝነት ማሳያ ናቸው። ተቋማችን ከፍተኛ የአሠራር ቅልጥፍና ከማረጋገጥ ባለፈ የተገጠመለት ቴክኖሎጂዎች የአካባቢ ጥበቃ መመሪያዎች ትግበራን የሚያቀላጥፉ ናቸው። የራክሲዮ ማዕከል ዲዛይን እና የመሳሪያ ምርጫዎች ከሀገሩ የአካባቢ እና የአየር ንብረት ሁኔታዎች ጋር የተጣጣሙ ናቸው፣ ይህም በኢትዮጵያ ያለው የራክሲዮ ተቋም በአፍሪካ አህጉር ተወዳዳሪ የሌለው የሃይል አጠቃቀም ብቃት (PUE) ሬሾ ላይ እንዲደርስ ያስችለዋል።

ለሚዲያ ጥያቄዎች ካላችሁ፡
ክላውዲያ ሩል
Raxio@axicom.com  

ስለ ራክሲዮ ዳታ ማዕከል 

ራክሲዮ ግሩፕ ከአፍሪካ ግንባር ቀደም የአገልግሎት አቅራቢገለልተኛ ደረጃ III የዳታ ማዕከል ኦፕሬተሮች አንዱ ሲሆን ተመራጭ የሆነ የኮሎኬሽን (Colocation) አገልግሎቶችን ያቀርባል። ... 2018 የተቋቋመ ሲሆን ለአፍሪካ ዲጂታል ኢኮኖሚ መሠረት የሆኑትን የኢንዱስትሪ ደረጃ የጠበቁ አገልግሎቶችን ማቅረብ ዓላማው ነው። በኡጋንዳ የመጀመሪያ ተቋም መከፈቱን ተከትሎ፣ ራክሲዮ በኢትዮጵያ፣ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ በኮትዲቩዋር፣ በታንዛኒያ፣ በሞዛምቢክ እና በአንጎላ ተስፋፍቷል። አሻራውን ያለማቋረጥ እያሰፋ ሲሆን በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ውስጥ በርካታ አዳዲስ ማዕከሎችን በመገንባት፣ በአፍሪካ አህጉር ውስጥ ንቁ ፍላጎቶችን የሚያሙዋላ፣ ትስስር ያለው የዳታ ማዕከል መረብ በመመስረት ላይ ይገኛል።

ለበለጠ መረጃ፣ እባክዎ www.raxiogroup.com ይጎብኙ።

ኤክስፐርቶቻችን/ሙያተኞቻችንን ያናግሩ

ስለ አገልግሎቶቻችን እና የራሲዮ የዳታ ማዕከላት/Raxio Data Centres እንዴት ለንግድ ስራዎ ድጋፍ ሊያደርጉልዎ እንደሚችሉ በተመለከተ የበለጠ ማወቅ ይፈልጋሉ? ለጥያቄዎችዎ በደስተኝነት መልስ ለመስጠት ዝግጁ ነን። ቅጾቹን ይሙሉ እና በተቻለ ፍጥነት እናገኝዎታለን።

ቆይ በናተህ...
ሁሉም ተጠናቀቀ!
ውይ! የሆነ ስህተት ተከስቷል. እባክዎ ዳግም ይሞክሩ.