አጋሮቻችን

የልህቀት አጋርነት

አገልግሎት መስጫዎቻችንና አገልግሎቶቻችን በመላው አፍሪካ አህጉር በደንበኞቻችን ልኬት ልክ ለማቅረብ እንዲረዳን ከአንዳንድ የአለማችን እጅግ ዝናን ያተረፉ ኩባንያዎች ጋር አብረን እንሰራለን። እነዚህ ኩበባንያዎች ለአፍሪካውያን ድርጅቶች እድገት፣ ፈጠራና ብልጽግና በምናደርገው እርዳታ ላይ ድጋፍ ያደርጉልናል።

በጥምር የቴክኒክ ሙያዊ ልምዳችን እና የአካባቢ ገበያ እውቀታችን እየታገዝን ከአፍሪካ ዲጂታል ኢኮኖሚ ጀርባ ያሉ አንቀሳቃሽ ሀይሎችን በጋራ በማገልገላችን ኩራት ይሰማናል።

Logo of Roha Group, an investment partner of Raxio's data centres in Africa

Roha Group

Roha Group መሰረቱን በዩኤስ ያደረገ በናይሮቢ፣ አዲስ አበባ፣ ዱባይ እና ኒውዮርክ ቢሮዎች ያሉት በመላው አፍሪካ ትርፋማ የንግድ ስራዎችን መመስረትን አድርጎ የሚሰራ የኢንቨስትመንት ድርጅት ነው። Roha በአፍሪካ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽ እምቅ አቅም እንዳለ በማመን በመላው አህጉሪቱ በአዳዲስ ኩባንያዎች ላይ ኢንቨስት ማድረግና መገንባት ላይ በኃላፊነት መስራቱን ቀጥሏል።

Roha ከሃሳብ መፍለቅና የንግድ ስራ እቅድ ዝግጅት ጀምሮ የካፒታል ኢንቨስትመንቶችን ማመንጨት እና የኩባንያዎቹን ስራዎች የንግድ እድገት እስከ መምራት ድረስ የአዳዲስ ኩባንያዎች ልማትን ይመራል።

Meridiam logo, an investment partner of Raxio's data centres in Africa

ሜሪዲያን/Meridiam

ሜሪዲያም/Meridiam የተመሰረተው በ2005 ዓ.ም በThierry Déau ዓላማውን የመንግስትና የግሉ ዘርፍ ፍላጎቶች ጥምረትን ለማህበረሰቦች የጋራ ፍላጎቶች ወሳኝ መፍትሔዎችን እንዲሰጡ ማስቻል አድርጎ ነበር። ሜሪዲያን በፈረንሳይ ሕግ እና የንብረት አስተዳደር ስር እራሱን የቻለ የኢንቨስትመንት ጥቅማ ጥቅም ኮርፖሬሽን ነው። ድርጅቱ በሶስት ዋና ዋና ዘርፎች ማለትም፡ በዘላቂ እንቅስቃሴ፣ ወሳኝ የህዝብ አገልግሎቶች እና የፈጠራ ዝቅተኛ የካርቦን ልቀት የቴክኖሎጂ ውጤቶች ልማት፣ በገንዘብ መደገፍና እና በዘላቂ የህዝብ መሰረተ ልማት የረጅም ጊዜ አስተዳደር ልዩ ሙያ አካብቷል። ሜሪዲያን በአሁኑ ወቅት ቢሮዎቹን በአዲስ አበባ፣ አማን፣ ዳካር፣ ኢስታንቡል፣ ጆሀንስበርግ፣ ሊበርቪል፣ ሉክሰምበርግ፣ ኒዮርክ፣ ፓሪስ፣ ቶሮንቶ እና ቪየና በመክፈት US$18 ቢሊዮን ሀብት እና ከ100 በላይ ፕሮጀክቶችን እያስተዳደረ ነው። ሜሪዲያን የISO 9001: 2015፣ በVigeoEiris (Moody) የተሰጠ የከፍተኛ ዘላቂነት ውጤት የብቃት ማረጋገጫን፣ የISO 37001 የAFNOR የጸረ ሙስና የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀትን ያገኘ ሲሆን ከESG እና የተባበሩት መንግስታት የዘላቂ ልማት ግቦችን (SDGs) መሰረት ያደረገ ተጽእኖ/ ውጤት ማምጣት ጋር በተያያዘ የባለቤትነት አሰራር ዘዴን ተግባራዊ ያደርጋል።

Logo of Future Tech, a technical partner of Raxio's data centres in Africa

Future-tech

Future-Tech መሰረቱን በዩኬ ያደረገ የዳታ ማዕከል ዲዛይን ሙያተኞች፣ የግንባታና ኮንስትራክሽን ሙያተኞች ስብስብ ነው። ባለው ከ30 አመታት በላይ ልምድ ታግዞ የFuture-Tech አጠቃላይ የአገልግሎት ፖርትፎሊዮ አድማሶች የፕሮጀክት አዋጭነትን፣ የሳይት ወይም አገልግሎት መስጫA ግዢና ልማትን፣ የንድፈ ሀሳብና የቴክኒክ ዲዛይንን፣ በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግና ማሻሻልን እና የቆይታ ዘመን የእቅድ ስርጭትን ጨምሮ አጠቃላይ የዳታ ማዕከል የቆይታ ዘመንን ያጠቃልላሉ።

Logo of Master Power, a technical partner of Raxio's data centres in Africa

Master Power

ማስተር ፖወር ቴክኖሎጂስ/Master Power Technologies ዋና መስሪያ ቤቱን በደቡብ አፍሪካ ያደረገ እና በናሚቢያ፣ ዛምቢያ፣ ሞዛምቢክ፣ ናይጄሪያ እና አንጎላ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤቶች ያሉት የግል ኩባንያ ነው። ማስተር ፖወር/Master Power አርክቴክቶችን፣ የኤሌክትሪክ እና የሜካኒካል መሀንዲሶችን ጨምሮ 9 በUptime Tier ማረጋገጫ ያገኙ ሙየተኞችን የያዘ የላቀ ችሎታ ያለው ቡድን በመያዝ በአፍሪካ ገበያ ውስጥ ለተዘጋጀ ሀይልና የዳታ ማዕከል የቴክኖሎጂ ውጤቶች ተስማሚ ሁኔታን ፈጥሯል። ከደንበኞች ጋር ባለው የረጅም ዘመን የአጋርነት እምነት እና ለሁሉም የቴክኖሎጂ ውጤቶቹ ጥገናና ሰርቪስ በማቅረብ ኩባንያው ዘላቂ የንግድ ስራ ሞዴልን በመገንባት በተከታታይ ለ3 ጊዜያት የFrost & Sullivan የዳታ ማዕከል ሽልማትን አግኝቷል።

ኤክስፐርቶቻችን/ሙያተኞቻችንን ያናግሩ

ስለ አገልግሎቶቻችን እና የራሲዮ የዳታ ማዕከላት/Raxio Data Centres እንዴት ለንግድ ስራዎ ድጋፍ ሊያደርጉልዎ እንደሚችሉ በተመለከተ የበለጠ ማወቅ ይፈልጋሉ? ለጥያቄዎችዎ በደስተኝነት መልስ ለመስጠት ዝግጁ ነን። ቅጾቹን ይሙሉ እና በተቻለ ፍጥነት እናገኝዎታለን።